Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 3:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እርስዋ ለሚመረኰዛት ሁሉ የሕይወት ዛፍ ናት፥ የሚታመኑባትም በእግዚአብሔር እንደ ጸና ሰው ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ለሚያቅፏት የሕይወት ዛፍ ናት፤ የሚይዟትም ይባረካሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እርሷ ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት፥ የተመረኰዘባትም ሁሉ ምስጉን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ጥበብ፥ ለሚይዟት ሰዎች ሕይወትን ትሰጣለች፤ እርስዋንም ገንዘብ የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 3:18
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለማ​የት ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን፥ ለመ​ብ​ላ​ትም መል​ካም የሆ​ነ​ውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከም​ድር አበ​ቀለ፤ በገ​ነ​ትም መካ​ከል የሕ​ይ​ወ​ትን ዛፍ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ሳ​የ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀ​ው​ንም ዛፍ አበ​ቀለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አለ፥ “እነሆ፥ አዳም መል​ካ​ም​ንና ክፉን ለማ​ወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁ​ንም እጁን እን​ዳ​ይ​ዘ​ረጋ፥ ደግ​ሞም ከሕ​ይ​ወት ዛፍ ወስዶ እን​ዳ​ይ​በላ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ሕያው ሆኖ እን​ዳ​ይ​ኖር፥”


ከጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ይወጣል። የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በድንገት ይወገዳሉ።


ከሚበለጽግና በተስፋ ከሚቈይ ሰውነቱን ሊረዳ የሚጀምር ይሻላል። መልካም ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ናት።


ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የሚጠብቀው ግን የዕውቀት መንፈስን ይሞላል።


ምክሬን ያዝ፥ አትተውም፤ ለራስህ ጠብቃት፥ እርሷ ሕይወትህ ናትና።


አሁንም ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ መንገዴን የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው።


የሚሰማኝ ሰው ብፁዕ ነው፥ መንገዴን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው፥ ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።


የጥ​በብ ጥላ ከብር ጥላ ይሻ​ላል፤ የጥ​በ​ብ​ንም ዕው​ቀት ማብ​ዛት ገን​ዘብ ላደ​ረ​ጋት ሕይ​ወ​ትን ትሰ​ጠ​ዋ​ለች።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።


በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ ዐሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች