Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 17:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 መማለጃን በዐመፃ በብብቱ የሚቀበል መንገዶቹን አያቀናም፥ ክፉ ሰውም ከጽድቅ መንገዶች ይርቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ክፉ ሰው ፍትሕ ለማዛባት፣ በስውር ጕቦ ይቀበላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ኀጥእ የፍርድን መንገድ ለማጥመም ከብብት መማለጃን ይወስዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ክፉ ሰው ፍርድን ለማጣመም፥ በምሥጢር ጉቦ ይቀበላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 17:23
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መማ​ለ​ጃን አት​ቀ​በል፤ መማ​ለጃ የዐ​ይ​ና​ማ​ዎ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ እው​ነ​ተኛ ቃል​ንም ያጣ​ም​ማ​ልና።


ትምህርት ገንዘብ ለሚያደርጓት የባለሟልነት ዋጋ ናት፥ ወደ ተመለሰችበትም መንገድን ታቀናለታለች።


ሀብት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ ከመኳንንት ጋርም ያኖረዋል።


በስውር ያለ ስጦታ ቍጣን ይመልሳል፥ ስጦታን የሚሸልግ ግን ጽኑ ቍጣን ያስነሣል።


ግፍ ጠቢ​ብን ያሳ​ብ​ደ​ዋል፥ የል​ቡ​ንም ትዕ​ግ​ሥት ያጠ​ፋ​ዋል።


አለ​ቆ​ችሽ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና የሌ​ቦች ባል​ን​ጀ​ሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወ​ድ​ዳሉ፤ ፍር​ድ​ንም ሊያ​ጣ​ምሙ ይፈ​ል​ጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይ​ፈ​ር​ዱም፤ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም አቤ​ቱታ አያ​ዳ​ም​ጡም።


በደ​ለ​ኛ​ውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ የጻ​ድ​ቁ​ንም ጽድቅ ለሚ​ያ​ስ​ወ​ግ​ዱ​በት ወዮ​ላ​ቸው!


በአ​ንቺ ውስጥ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ መማ​ለ​ጃን ተቀ​በሉ፤ በአ​ን​ቺም አራ​ጣና ትርፍ ወስ​ደ​ዋል፤ ቀማ​ኛ​ነ​ት​ሽ​ንና ኀጢ​አ​ት​ሽን ፈጸ​ምሽ፤ እኔ​ንም ረሳ​ሽኝ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በው​ስ​ጥዋ ያሉ አለ​ቆ​ችዋ የስ​ስ​ትን ትርፍ ለማ​ግ​ኘት ሲሉ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ፥ ነፍ​ሶ​ች​ንም ያጠፉ ዘንድ እን​ደ​ሚ​ና​ጠቁ ተኵ​ላ​ዎች ናቸው።


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።


ፍርድን የምትጠሉ ቅን ነገርንም ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ።


እጆቻቸውን ለክፋት ያነሣሉ፥ አለቃውና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፥ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጕናሉ።


ፍር​ድን አታ​ጣ​ምም፤ ፊት አይ​ተ​ህም አታ​ድላ፤ ጉቦን አት​ቀ​በል፥ ጉቦ የጥ​በ​በ​ኞ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ቃል ያጣ​ም​ማ​ልና ጉቦ አት​ቀ​በል።


እነ​ሆኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና እርሱ በቀ​ባው ፊት መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ የማ​ንን በሬ ወሰ​ድሁ? የማ​ን​ንስ አህያ ወሰ​ድሁ? ማን​ንስ ሸነ​ገ​ልሁ? በማ​ንስ ላይ ግፍ አደ​ረ​ግሁ? ነጠላ ጫማ እን​ኳን ቢሆን ከማን እጅ መማ​ለጃ ተቀ​በ​ልሁ? መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ እኔ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”


ልጆ​ቹም በመ​ን​ገዱ አል​ሄ​ዱም፤ ነገር ግን ረብ ለማ​ግ​ኘት ፈቀቅ አሉ፤ መማ​ለጃ በሉ፤ ፍርድ አደሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች