Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 15:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እግዚአብሔር የትዕቢተኞችን ቤት ያፈርሳል፤ የመበለቷን ወሰን ግን ያጸናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እግዚአብሔር የትዕቢተኛውን ቤት ያፈርሰዋል፤ የመበለቲቱን ዳር ድንበር ግን እንዳይደፈር ይጠብቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ጌታ የትዕቢተኞችን ቤት ይነቅላል፥ የባልቴትን ዳርቻ ግን ያጸናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እግዚአብሔር የትዕቢተኞችን ቤት ይደመስሳል፤ ባልዋ የሞተባትን ሴት ድንበር እንዳይገፋ ይጠብቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 15:25
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለማ​ት​ወ​ል​ደው ለመ​ካ​ኒቱ በጎ​ነ​ትን አላ​ደ​ረ​ገ​ላ​ትም፤ ለም​ት​ወ​ል​ደ​ውም አል​ራ​ራም።


ዕው​ቀ​ትህ በእኔ ላይ ተደ​ነ​ቀች፤ በረ​ታ​ች​ብኝ፥ ወደ እር​ሷም ለመ​ድ​ረስ አል​ች​ልም።


ለእ​ን​ስ​ሶ​ችና ለሚ​ጠ​ሩት ለቍ​ራ​ዎች ጫጩ​ቶች፥ ምግ​ባ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ጣ​ቸው እርሱ ነው።


ሰነፍ በልቡ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለም ይላል። ረከሱ፥ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም ጐሰ​ቈሉ፤ በጎ ነገ​ርን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ዞ​ችን አጥ​ን​ቶች በት​ኖ​አ​ልና በዚያ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ሳይ​ኖር እጅግ ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ቸ​ዋ​ልና አፈሩ።


ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥ የጻድቃን ቤቶች ግን ጸንተው ይኖራሉ።


የክፉዎች ቤቶች ይፈርሳሉ፤ የቅኖች ማደሪያዎች ግን ይጸናሉ።


ዐመፃን ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ የተናቀ ነው፤ የንጹሓን ቃል ግን ያማረ ነው።


አባቶችህ ያኖሩትን የድንበር ምልክት አታፍልስ፤ ወደ ድሃ አደጎች እርሻም አትግባ፤


መል​ካም መሥ​ራ​ትን ተማሩ፤ ፍር​ድን ፈልጉ፤ የተ​ገ​ፋ​ውን አድኑ፤ ለድ​ሃ​አ​ደጉ ፍረ​ዱ​ለት፤ ስለ መበ​ለ​ቲ​ቱም ተሙ​አ​ገቱ።”


የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በት​ዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውና በኵ​ራ​ተ​ኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለ​ውም ላይ ይሆ​ናል፤ እነ​ር​ሱም ይዋ​ረ​ዳሉ፤


ፍር​ድን አጣ​መሙ ለድ​ሃ​አ​ደ​ጎች ፍር​ድን አል​ፈ​ረ​ዱም፤ ለመ​በ​ለ​ቷም አል​ተ​ሟ​ገ​ቱም።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር፤ በም​ት​ካ​ፈ​ላት ርስ​ትህ አባ​ቶ​ችህ የተ​ከ​ሉ​ትን የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህን የድ​ን​በር ምል​ክት አት​ን​ቀል።


ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።


እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች