Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 መንገዳቸው ቀና የሆነውን የዋሃንን ጽድቅ ትጠብቃቸዋለች፤ ኀጢአተኞችን ግን ኀጢአታቸው በደለኛ ታደርጋቸዋለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ጽድቅ ቅን የሆነውን ሰው ትጠብቀዋለች፤ ክፋት ግን ኀጢአተኛውን ትጥለዋለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በመንገዱ ያለ ነውር የሚሄደውን ጽድቅ ይጠብቀዋል፥ ኃጢአት ግን ኃጢአተኛውን ይጥለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ደጋግ ሰዎች ደግነታቸው ይጠብቃቸዋል፤ ኃጢአተኞችን ግን ኃጢአታቸው ያጠፋቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 13:6
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰሎ​ሞ​ንም፥ “እርሱ አካ​ሄ​ዱን ያሳ​መረ እንደ ሆነ ከእ​ርሱ አን​ዲት ጠጕር እንኳ በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም፤ ነገር ግን ክፋት የተ​ገ​ኘ​በት እንደ ሆነ ይሞ​ታል” አለ።


ይህም ነገር ከገጸ ምድር ለመ​ፍ​ረ​ስና ለመ​ጥ​ፋት በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ ኀጢ​አት ሆነ።


ንጉ​ሡም፥ “የመ​ቱ​ኝን የደ​ማ​ስ​ቆን አማ​ል​ክት እፈ​ል​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የሶ​ር​ያን ንጉሥ እር​ሱን ረድ​ተ​ው​ታ​ልና እኔ​ንም ይረ​ዱኝ ዘንድ እሠ​ዋ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለ። ነገር ግን ለእ​ር​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዕን​ቅ​ፋት ሆኑ።


አቤቱ፥ በተ​ጨ​ነ​ቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ሰማ​ኸ​ኝም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ሁት፥ “አንተ ጌታዬ ነህ፤ በጎ​ነ​ቴን አት​ሻ​ት​ምና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ራ​ል​ኛል፥ ያድ​ነ​ኛ​ልም፤ ምን ያስ​ፈ​ራ​ኛል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ይ​ወቴ መታ​መ​ኛዋ ነው፤ ምን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ኛል?


እግዚአብሔርን መፍራት ለደግ ሰው ብርታት ነው፥ ጥፋት ግን ክፋት ለሚያደርጉ ነው።


ጠማማ መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን በፊቱ የተመረጡ ናቸው።


ጻድቃንን ፍጻሜያቸው ትመራቸዋለች፤ ኃጥኣንን ግን መሰነካከላቸው ትማርካቸዋለች።


የክፉዎች ልብ ጽድቅን አያውቅም፥ ክፋትም ኃጥአንን ያከፋቸዋል።


ኀጢአት ሰውን ያጠምዳል፥ ሁሉም በኀጢአቱ ልባብ ይታሰራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች