Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 12:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ራሱን የሚያውቅ ሰው ለራሱ ጻድቅ ነው፤ የክፉዎች ሥራ ግን መልካም አይደለም። የሚበድሉ ሰዎችን ክፉ ይከተላቸዋል፥ የኃጥኣን መንገዳቸውም ታስታቸዋለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ጻድቅ ሰው ለወዳጁ መልካም ምክር ይሰጣል፤ የክፉዎች መንገድ ግን ወደ ስሕተት ይመራቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ጻድቅ ለባልንጀራው መንገዱን ያሳያል፥ የኀጥኣን መንገድ ግን ታስታቸዋለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እውነተኛ ሰው ወዳጁን በመምከር ወደ ቅን መንገድ ይመራዋል፤ የዐመፀኞች መንገድ ግን ከእውነት የሚያርቅ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 12:26
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሌ​ሊ​ትም ጐበ​ኘ​ኸኝ፤ ልቤ​ንም ፈተ​ን​ኸው፥ ፈተ​ን​ኸኝ፥ ዐመ​ፅም አል​ተ​ገ​ኘ​ብ​ኝም።


ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።


የሚያስደነግጥ ቃል የጻድቅ ሰው ልቡናን ያውካል፤ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።


ታካች ሰው አድኖ አይዝም። ንጹሕ ሰው ግን ክቡር ሀብት ነው።


ስሕተተኞች ክፉን ያስባሉ፤ ደጋጎች ግን ምሕረትንና እውነትን ያስባሉ። ክፋትንም የሚሠሩ ምሕረትንና ይቅርታን አያውቁም። ነገር ግን ታማኝነትና ቸርነት ደግ በሚሠሩ ዘንድ ናቸው።


ክፉ ሰው ወዳጆቹን ይዋሻል፥ መልካምም ወዳልሆኑ መንገዶች ይመራቸዋል።


ሻካራ ቃልን ከመናገር የሚከለክል ዐዋቂ ነው፥ ትዕግሥተኛ ሰውም ብልህ ነው።


ስለሚያስቱአችሁ ሰዎች ይህን ጽፌላችኋለሁ።


ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።


በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች