ፊልጵስዩስ 4:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 አሁንም የተወደዳችሁና የምናፍቃችሁ ወንድሞቻችን ሆይ፥ ደስታችንና አክሊላችን ናችሁ፤ ወዳጆቻችን ሆይ፥ እንዲህ ቁሙ፤ በጌታችንም ጽኑ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ስለዚህ የምወድዳችሁና የምናፍቃችሁ፣ ወንድሞቼ ደስታዬና አክሊሌ የሆናችሁ፣ እንዲሁም ወዳጆች ሆይ፤ በዚህ ሁኔታ በጌታ ጸንታችሁ ቁሙ! ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ስለዚህ የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ደስታዬና አክሊሌ ናችሁ፤ የተወደዳችሁ ሆይ! በዚህ መንገድ በጌታ ጸንታችሁ ቁሙ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ፥ የደስታዬና የሥራዬ አክሊል የሆናችሁ ወንድሞቼ ሆይ! በጌታ ጸንታችሁ ኑሩ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ስለዚህ፥ የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ፥ ደስታዬና አክሊሌ የምትሆኑ ወንድሞቼ ሆይ፥ እንዲሁ በጌታ ቁሙ፥ ወዳጆች ሆይ። ምዕራፉን ተመልከት |