Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ፊልሞና 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባሪያ አይሆንም፤ ነገር ግን ለእኔ በተለየ የተወደደ ወንድም ከሆነ፥ ለአንተማ ይልቅ በሥጋውም በጌታም ዘንድ ከባሪያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከእንግዲህ ወዲህ ግን እንደ ባሪያ ሳይሆን ከባሪያ በላይ የሆነ ተወዳጅ ወንድም ነው። ለእኔ ተወዳጅ ነው፤ ለአንተ ግን በሥጋም በጌታም ይበልጥ ተወዳጅ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባርያ አይሆንም፤ ነገር ግን ለእኔ በተለየ የተወደደ ወንድም ከሆነ፥ ለአንተማ ይልቅ በሥጋውም ሆነ በጌታ ዘንድ ከባርያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከእንግዲህ ወዲህ ከአንተ ጋር የሚኖረውም እንደ ባሪያ ሳይሆን ከባሪያ የበለጠ ሆኖ እንደ ውድ ወንድም ነው፤ እርሱ ለእኔ ውድ ወንድም ነው፤ ይሁን እንጂ በሥጋ እርሱ በአገልግሎቱ ስለሚጠቅምህ በመንፈሱ ደግሞ በክርስቶስ ወንድምህ ስለ ሆነ ለአንተ ይበልጥ ተወዳጅ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባሪያ አይሆንም፥ ነገር ግን ለእኔ በተለየ የተወደደ ወንድም ከሆነ፥ ለአንተማ ይልቅ በስጋውም በጌታም ዘንድ ከባሪያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ፊልሞና 1:16
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እናንተ ግን ‘መምህር’ ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።


ያን​ጊ​ዜም ሐና​ንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁ​ንም ጫነ​በ​ትና፥ “ወን​ድሜ ሳውል፥ በመ​ን​ገድ ስት​መጣ የታ​የህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ታይና መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​ብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮ​ኛል” አለው።


የተ​ጠራ ባሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነጻ​ነት ያለው ነውና፤ እን​ዲሁ ነጻ​ነት ያለ​ውም ከተ​ጠራ የክ​ር​ስ​ቶስ ባርያ ነው።


አገ​ል​ጋ​ዮች ሆይ በቅን ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት እንጂ ለሰው ደስ እን​ደ​ም​ታ​ሰኙ ለታ​ይታ የም​ት​ገዙ ሳት​ሆኑ፥ በሥጋ ጌቶ​ቻ​ችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ።


የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ።


አሁ​ንም ከሰ​ማ​ያዊ ጥሪ ተካ​ፋ​ዮች የሆ​ና​ችሁ ቅዱ​ሳን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ንን ሐዋ​ር​ያና ሊቀ ካህ​ናት ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ተመ​ል​ከቱ።


ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች