Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 31:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሙሴም አላ​ቸው፥ “ሴቶ​ችን ሁሉ ለምን አዳ​ና​ች​ኋ​ቸው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሙሴም እንዲህ አላቸው፤ “ሴቶችን ሁሉ እንዴት በሕይወት ትተዉአቸዋላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሙሴም አላቸው፦ “በውኑ ሴቶችን ሁሉ በሕይወት እንዲኖሩ ፈቀዳችሁላቸውን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እንዲህም ሲል ጠየቃቸው፦ “ሴቶችን በሙሉ በሕይወት ያስቀራችሁት ለምንድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሙሴም አላቸው፦ በውኑ ሴቶችን ሁሉ አዳናችኋቸውን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 31:15
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ በቸ​ልታ የሚ​ያ​ደ​ርግ ርጉም ይሁን፤ ሰይ​ፉ​ንም ከደም የሚ​ከ​ለ​ክል ርጉም ይሁን።


ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንና ጎበ​ዙን፥ ድን​ግ​ሊ​ቱ​ንም፥ ሕፃ​ና​ቱ​ንና ሴቶ​ቹን፥ ፈጽ​ማ​ችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምል​ክቱ ወደ አለ​በት ሰው ሁሉ አት​ቅ​ረቡ፤ በመ​ቅ​ደ​ሴም ጀምሩ” አላ​ቸው። በቤ​ቱም አን​ጻር ባሉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጀመሩ።


ሙሴም ከዘ​መቻ በተ​መ​ለ​ሱት በጭ​ፍራ አለ​ቆች፥ በሻ​ለ​ቆ​ችና በመቶ አለ​ቆች ላይ ተቈጣ።


በዚ​ያን ጊዜም ከተ​ሞ​ቹን ሁሉ ወሰ​ድን፤ ከተ​ማ​ው​ንም ሁሉ፥ ሴቶ​ች​ንም፥ ሕፃ​ኖ​ች​ንም አጠ​ፋን፤ አን​ዳ​ችም የሸሸ በሕ​ይ​ወት አላ​ስ​ቀ​ረ​ንም፥


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ አሳ​ልፎ በሰ​ጣት ጊዜ፥ በእ​ር​ስዋ ያሉ​ትን ወን​ዶች ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት ትገ​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤


ከሴ​ቶ​ቹና ከጓዙ በቀር እን​ስ​ሶ​ቹን፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ያለ​ውን ምርኮ ሁሉ ዘር​ፈህ ለአ​ንተ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የጠ​ላ​ቶ​ች​ህን ምርኮ ትበ​ላ​ለህ።


እን​ዲ​ሁም ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ፥ ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር፥ ደቡ​ቡ​ንም፥ ቆላ​ው​ንም፥ ቍል​ቍ​ለ​ቱ​ንም፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ መታ፤ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘ​ውም ነፍስ ያለ​በ​ትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የእ​ነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ምርኮ ሁሉ፥ ከብ​ቶ​ቹ​ንም ለራ​ሳ​ቸው ዘረፉ፤ ሰዎ​ቹን ሁሉ ግን እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያለ​ው​ንም ሁሉ አን​ድም አላ​ስ​ቀ​ሩም።


ኢያ​ሱም ከተ​ማ​ዋን፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ውስጥ የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ፥ ከወ​ንድ እስከ ሴት፥ ከሕ​ፃን እስከ ሽማ​ግሌ፥ ከበሬ እስከ በግና እስከ አህያ በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋ።


በዚ​ያም ቀን የወ​ደ​ቁት ሁሉ ወን​ድም፥ ሴትም፥ የጋይ ሰዎች ሁሉ ዐሥራ ሁለት ሺህ ነፍስ ነበሩ።


አሁ​ንም ሄደህ አማ​ሌ​ቅ​ንና ኢያ​ሬ​ምን ምታ፤ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፈጽ​መህ አጥፋ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የም​ታ​ድ​ነው የለም። አጥ​ፋ​ቸው፤ መከ​ራም አጽ​ና​ባ​ቸው፤ የእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያ​ቸ​ውም፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ወን​ዱ​ንና ሴቱን፥ ብላ​ቴ​ና​ው​ንና ሕፃ​ኑን፥ በሬ​ው​ንና በጉን፥ ግመ​ሉ​ንና አህ​ያ​ውን ግደል።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች