Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 31:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የማ​ረ​ኩ​ትን ምር​ኮ​ው​ንና የዘ​ረ​ፉ​ትን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ወዳ​ለው ሰፈር አመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የማረኳቸውን ሰዎች፣ የነዷቸውን እንስሳትና የዘረፉትን ሀብት በሙሉ፣ ከኢያሪኮ ማዶ፣ በዮርዳኖስ አጠገብ፣ በሞዓብ ወዳለው፣ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር እንዲሁም መላው የእስራኤላውያን ማኅበር ወዳሉበት ሰፈራቸው አመጧቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የማረኩአቸውንም ሰዎች ምርኮውንና ብዝበዛውን፥ በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር፥ ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር አመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ ትይዩ በሞአብ ሜዳ ላይ ሰፍረው ወደነበሩት ወደ ሙሴና ወደ አልዓዛር እንዲሁም ወደ መላው ማኅበር አመጡአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የማረኩአቸውንም ሰዎች ምርኮውንና ብዝበዛውን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር፥ በዮርዳኖስም አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር አመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 31:12
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጓዙ፤ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በሞ​ዓብ ምዕ​ራ​ብም ሰፈሩ።


ከሰው እስከ እን​ስሳ ምር​ኮ​አ​ቸ​ው​ንና ብዝ​በ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ ወሰዱ።


ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም፥ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ሊገ​ና​ኙ​አ​ቸው ወጡ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የእ​ነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ምርኮ ሁሉ፥ ከብ​ቶ​ቹ​ንም ለራ​ሳ​ቸው ዘረፉ፤ ሰዎ​ቹን ሁሉ ግን እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያለ​ው​ንም ሁሉ አን​ድም አላ​ስ​ቀ​ሩም።


ነገር ግን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ የና​ስና የብ​ረ​ትም ዕቃ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሁን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግምጃ ቤት ይግባ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች