Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 30:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ባልዋ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ስእ​ለ​ቷን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስለ ስእ​ለቷ ወይም ራስ​ዋን ስላ​ሰ​ረ​ች​በት መሐላ ከአ​ፍዋ የወ​ጣው ነገር አይ​ጸ​ናም፤ ባልዋ ከል​ክ​ሏ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያነ​ጻ​ታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ባሏ ሰምቶ እንዲቀሩ ካደረገ ግን ስእለቶቿንም ሆነ ለማድረግ ቃል የገባቻቸውን ነገሮች የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ባሏ እንዲቀሩ ስላደረጋቸው እግዚአብሔር ነጻ ያደርጋታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ከንቱ ቢያደርገው፥ ስለ ስእለትዋ ወይም ራስዋን ስላሰረችበት መሐላ በአንደበትዋ የተናገረችው ማናቸውም ነገር አይጸናም፤ ባልዋ ከንቱ አድርጎታል፤ ጌታም ይቅር ይላታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ስእለትዋን እንዳትፈጽም ቢከለክላት ግን የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው ባልዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ከንቱ ቢያደርገው፥ ስለ ስእለትዋ ወይም ራስዋን ስላሰረችበት መሐላ ከአፍዋ የወጣው ነገር አይጸናም፤ ባልዋ ከንቱ አድርጎታል፤ እግዚአብሔርም ይቅር ይላታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 30:12
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን እኛና አባ​ቶ​ቻ​ችን፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ እና​ደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ ከአ​ፋ​ችን የወ​ጣ​ውን ቃል ሁሉ በር​ግጥ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ በዚያ ጊዜም እን​ጀ​ራን እን​ጠ​ግብ ነበር፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ልን ነበር፤ ክፉም አና​ይም ነበር።


እኛስ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት ባጠ​ን​ን​ላት፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን ባፈ​ሰ​ስ​ን​ላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎ​ቻ​ችን ምስ​ል​ዋን ለማ​በ​ጀት እን​ጎቻ አድ​ር​ገ​ን​ላት ኖሮ​አ​ልን? የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን አፍ​ስ​ሰ​ን​ላት ኖሮ​አ​ልን?”


ካህ​ኑም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ ባለ​ማ​ወቅ ነበ​ርና ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ እነ​ር​ሱም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውና ስላ​ለ​ማ​ወ​ቃ​ቸው ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባሉ።


ካህ​ኑም ባለ​ማ​ወቅ ስለ በደ​ለው ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ባለ​ማ​ወ​ቅም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ስለ ሠራው ሰው ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።


ባል​ዋም ሰምቶ ዝም ቢላት፥ ባይ​ከ​ለ​ክ​ላ​ትም፥ ስእ​ለቷ ሁሉ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ ሁሉ ይጸ​ናል።


“ስእ​ለ​ቷን ሁሉ፥ ነፍ​ስ​ዋ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ውን የመ​ሐላ ማሰ​ሪያ ሁሉ ባልዋ ያጸ​ና​ዋል፤ ወይም ባልዋ ይከ​ለ​ክ​ለ​ዋል።


አባቷ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስእ​ለቷ፥ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐ​ላዋ አይ​ጸ​ኑም፤ አባቷ ከል​ክ​ሎ​አ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ይላ​ታል።


ባልዋ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስእ​ለ​ቷና ራስ​ዋን ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ አይ​ጸ​ኑም፤ ባልዋ ከል​ክ​ሎ​አ​ታ​ልና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይቅር ይላ​ታል።


ነገር ግን የወ​ንድ ሁሉ ራሱ ክር​ስ​ቶስ፥ የሴ​ትም ራስዋ ወንድ፤ የክ​ር​ስ​ቶ​ስም ራሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ልታ​ውቁ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።


ባል​ዋም ሕል​ቃና፥ “በዐ​ይ​ንሽ ደስ ያሰ​ኘ​ሽን አድ​ርጊ፤ ጡትም እስ​ኪ​ተው ድረስ ተቀ​መጪ፤ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ፍሽ የወ​ጣ​ውን ያጽና” አላት። ሴቲ​ቱም ልጅ​ዋን እያ​ጠ​ባች ጡት እስ​ኪ​ተው ድረስ ተቀ​መ​ጠች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች