Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 3:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵ​ሮች ገን​ዘ​ቡን ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ አም​ስት ዲድ​ር​ክም እንደ መቅ​ደሱ ዲድ​ር​ክም ሚዛን ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 ከእስራኤላውያን በኵሮች ላይ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ልክ አንድ ሺሕ ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ሰቅል ሰበሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 ከእስራኤል ልጆች በኵራት አንድ ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ አምስት ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ገንዘቡን ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 ከእስራኤላውያን በኲሮች በመቅደሱ ሚዛን መሠረት ገንዘቡን አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሥልሳ አምስት ሰቅል ብር ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 ከእስራኤል ልጆች በኵሮች ገንዘቡን ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ወሰደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 3:50
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙሴም በሌ​ዋ​ው​ያን ከተ​ቤ​ዡት በላይ ከተ​ረ​ፉት ዘንድ የመ​ቤ​ዣ​ውን ገን​ዘብ ወሰደ።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ የመ​ቤ​ዣ​ውን ገን​ዘብ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ሰጠ።


እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


የዘ​ለ​ዓ​ለም መድ​ኀ​ኒ​ትን ገን​ዘብ አድ​ርጎ፥ በገዛ ደሙ አንድ ጊዜ ወደ መቅ​ደስ ገባ እንጂ በላ​ምና በፍ​የል ደም አይ​ደ​ለም።


ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።


ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች