Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እባ​ክህ፥ በም​ድ​ርህ ላይ እን​ለፍ፤ ወደ እር​ሻም ወደ ወይ​ንም አን​ገ​ባም፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዶ​ችም ውኃን አን​ጠ​ጣም፤ በን​ጉሡ ጎዳና እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ዳር​ቻ​ህ​ንም እስ​ክ​ና​ልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አን​ልም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ በአገርህ እንድናልፍ እባክህን ፍቀድልን፤ በየትኛውም ዕርሻ ወይም የወይን ተክል ውስጥ አንገባም፤ ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። የንጉሡን አውራ ጐዳና ይዘን ከመጓዝ በቀር፣ ግዛትህን ዐልፈን እስክንሄድ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፥ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፥ ከጉድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጐዳና እንሄዳለን፥ ግዛትህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህ በምድርህ አልፈን እንድንሄድ እባክህ ፍቀድልን፤ እኛም ሆንን ከብቶቻችን ከመንገድ ውጪ አንወጣም፤ ወደ እርሻዎችህም ሆነ ወደ ወይን ተክሎችህ አንገባም፤ ከውሃ ጒድጓዶችህም አንጠጣም፤ ግዛትህን እስክናልፍ ድረስ ከዋናው መንገድ አንወጣም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፥ ከጕድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጐዳና እንሄዳለን፥ ዳርቻህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 20:17
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁ​ንም እነሆ፥ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብዕ ምድር በወጡ ጊዜ ያል​ፉ​ባ​ቸው ዘንድ ያል​ፈ​ቀ​ድ​ህ​ላ​ቸው የአ​ሞ​ንና የሞ​ዓብ ልጆች፥ የሴ​ይ​ርም ተራራ ሰዎች እን​ዳ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ፈቀቅ ብለው ነበር።


በአ​ዜብ በኩል ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረው ከነ​ዓ​ና​ዊው የአ​ራድ ንጉሥ በአ​ታ​ሪን መን​ገድ እስ​ራ​ኤል እንደ መጡ ሰማ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ሰልፍ አደ​ረገ ከእ​ነ​ር​ሱም ምርኮ ማረከ።


‘በሀ​ገ​ርህ ላይ ልለፍ፤ በአ​ውራ ጎዳና እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አል​ተ​ላ​ለ​ፍም።


የም​በ​ላ​ውን ምግብ በገ​ን​ዘብ ሽጥ​ልኝ፤ የም​ጠ​ጣ​ው​ንም ውኃ በገ​ን​ዘብ ስጠኝ፤ በእ​ግሬ ብቻ ልለፍ፤


በሴ​ይር የተ​ቀ​መጡ የዔ​ሳው ልጆች፥ በአ​ሮ​ዔ​ርም የተ​ቀ​መጡ ሞዓ​ባ​ው​ያን እን​ዳ​ደ​ረ​ጉ​ልኝ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጠን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን እስ​ክ​ሻ​ገር ድረስ በእ​ግሬ ልለፍ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች