Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 16:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እነ​ር​ሱም፥ ለእ​ነ​ር​ሱም የነ​በሩ ሁሉ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድ​ሪ​ቱም ተዘ​ጋ​ች​ባ​ቸው፤ ከማ​ኅ​በ​ሩም መካ​ከል ጠፉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እነርሱም ካላቸው ከማናቸውም ነገር ጋራ ከነሕይወታቸው ወደ መቃብር ወረዱ፤ ምድሪቱም በላያቸው ተከደነችባቸው፤ ጠፉ፤ ከማኅበረ ሰቡም ተወገዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እነርሱም የእነርሱም የሆነው ሁሉ በሕይወታቸው ሳሉ ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ላይ ተዘጋችባቸው፥ ከጉባኤውም መካከል ጠፉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ስለዚህ በሕይወት ሳሉ ከነንብረታቸው ወደ ሙታን ዓለም ወረዱ፤ ምድርም በላያቸው ተከድና ጠፉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እነርሱም ለእነርሱም የነበሩ ሁሉ በሕይወታቸው ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም ተዘጋችባቸው፥ ከጉባኤውም መካከል ጠፉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 16:33
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ ስም​ህን አመ​ሰ​ግን ዘንድ ሰው​ነ​ቴን ከእ​ሥ​ራት አው​ጣት፤ ዋጋ​ዬን እስ​ክ​ት​ሰ​ጠኝ ድረስ ጻድ​ቃን እኔን ይጠ​ብ​ቃሉ።


እጅ​ህን ከአ​ር​ያም ላክ፥ ከብዙ ውኃም አድ​ነኝ፤ ከባ​ዕድ ልጆ​ችም እጅ፥


አሕ​ዛብ በሠ​ሩት በደ​ላ​ቸው ጠፉ፥ በዚ​ያ​ችም በሸ​ሸ​ጓት ወጥ​መድ እግ​ራ​ቸው ተጠ​መደ።


ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወ​ድ​ቃ​ለህ፤ ወደ ምድር ጥል​ቅም ትወ​ር​ዳ​ለህ።


“ሲኦ​ልም በመ​ም​ጣ​ትህ ልት​ገ​ና​ኝህ በታች ታወ​ከች፤ የአ​ሕ​ዛ​ብን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ከዙ​ፋ​ና​ቸው ያስ​ነሡ፥ ምድ​ርን የገ​ዙ​አት አር​በ​ኞች ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት በአ​ንተ ላይ ተነሡ።


በመ​ቃ​ብር የሚ​ኖሩ አያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​ህ​ምና፤ ሙታ​ንም የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑህ አይ​ደ​ሉ​ምና፤ በሲ​ኦ​ልም የሚ​ኖሩ ይቅ​ር​ታ​ህን ተስፋ አያ​ደ​ር​ጉ​ምና።


በው​ኃው አጠ​ገብ ያሉ የዕ​ን​ጨ​ቶች ሁሉ ቁመት እን​ዳ​ይ​ረ​ዝም ራሱም ወደ ደመና እን​ዳ​ይ​ደ​ርስ ያንም ውኃ የሚ​ጠ​ጡት እን​ጨ​ቶች ሁሉ በር​ዝ​መ​ታ​ቸው ከእ​ርሱ ጋራ እን​ዳ​ይ​ተ​ካ​ከሉ ሁሉም ወደ መቃ​ብር በሚ​ወ​ርዱ ሰዎች መካ​ከል በጥ​ልቅ ምድር ሞቱ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ኀይል ዋይ በል፤ እር​ስ​ዋ​ንና የብ​ር​ቱ​ዎ​ቹን አሕ​ዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ወደ ታች​ኛው ምድር ጣላ​ቸው።


ከአ​ል​ተ​ገ​ረ​ዙና ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ተኝ​ተ​ዋል፤ የሰ​ሜን አለ​ቆች ሁሉ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ወር​ደው በዚያ አሉ፤ በኀ​ይ​ላ​ቸ​ውም ያስ​ፈሩ በነ​በ​ረው ፍር​ሀት አፍ​ረ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ያል​ተ​ገ​ረ​ዙት ተኝ​ተ​ዋል፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ር​ዱት ጋር ቅጣ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ክ​መ​ዋል።


ምድ​ሪ​ቱም አፍ​ዋን ከፍታ እነ​ር​ሱን፥ ቤተ ሰቦ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ለቆ​ሬም የነ​በ​ሩ​ትን ሰዎች ሁሉ፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ዋጠ​ቻ​ቸው።


በዙ​ሪ​ያ​ቸው የነ​በሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ከጩ​ኸ​ታ​ቸው የተ​ነሣ፥ “ምድ​ሪቱ እን​ዳ​ት​ው​ጠን” ብለው ሸሹ።


አህ​ያ​ዪ​ቱም አይ​ታኝ ከፊቴ ፈቀቅ አለች፤ ይህም ሦስ​ተኛ ጊዜ ነው፤ ከፊ​ቴስ ፈቀቅ ባላ​ለች በእ​ው​ነት አሁን አን​ተን በገ​ደ​ል​ሁህ፤ እር​ሷ​ንም ባዳ​ን​ኋት ነበር” አለው።


የቆሬ ልጆች ግን አል​ሞ​ቱም።


እሳት ከቍ​ጣዬ ትነ​ድ​ዳ​ለ​ችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ር​ንም ከፍ​ሬዋ፤ ጋር ትበ​ላ​ለች፤ የተ​ራ​ሮ​ችን መሠ​ረት ታነ​ድ​ዳ​ለች።


ወዮላቸው! በቃየል መንገድ ሄደዋልና፤ ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል፤ በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች