Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 16:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “ሁሉን በቅ​ጽ​በት አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ከዚህ ማኅ​በር መካ​ከል ፈቀቅ በሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “ሁሉንም በአንድ ጊዜ እንዳጠፋቸው እናንተ ከዚህ ማኅበር ተለዩ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 “ሁሉንም በአንድ ጊዜ ስለማጠፋቸው ከዚህ ማኅበር መካከል ተለዩ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ከእነዚህ ሕዝብ ራቅ ብላችሁ ቁሙ፤ እኔም እነርሱን በአንድ ጊዜ እደመስሳቸዋለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሁሉን በቅጽበት አጠፋቸው ዘንድ ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 16:21
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኛ ይህ​ችን ስፍራ እና​ጠ​ፋ​ታ​ለ​ንና፥ ጩኸ​ታ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትልቅ ሆኖ​አ​ልና፤ እና​ጠ​ፋ​ትም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልኮ​ናል።”


ሎጥም ወጣ፤ ልጆ​ቹን ለሚ​ያ​ገ​ቡት ለአ​ማ​ቾ​ቹም አላ​ቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ከተማ ያጠ​ፋ​ታ​ልና።” ለአ​ማ​ቾቹ ግን የሚ​ያ​ፌ​ዝ​ባ​ቸው መሰ​ላ​ቸው።


የም​ት​ገ​ዛ​ል​ህን ነፍስ ለአ​ራ​ዊት አት​ስ​ጣት፤ የድ​ሆ​ች​ህ​ንም ነፍስ ለዘ​ወ​ትር አት​ርሳ።


አሁ​ንም ተቈ​ጥቼ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ተወኝ፤ አን​ተ​ንም ለታ​ላቅ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።”


ግብ​ፃ​ው​ያ​ንስ፦ ‘በተ​ራራ መካ​ከል ሊገ​ድ​ላ​ቸው፥ ከም​ድ​ርም ፊት ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው ለክ​ፋት አወ​ጣ​ቸው’ ብለው ስለ ምን ይና​ገ​ራሉ? ከመ​ዓ​ትህ ተመ​ለስ፤ ለሕ​ዝ​ብ​ህም በክ​ፋ​ታ​ቸው ላይ ራራ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እና​ንተ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ ናችሁ፤ ሌላ መቅ​ሠ​ፍት እን​ዳ​ላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁና እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ አሁ​ንም የክ​ብር ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንና ጌጣ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ አውጡ፤ የማ​ደ​ር​ግ​ባ​ች​ሁ​ንም አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ በላ​ቸው” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወጣ፤ ከአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም ሰፈር መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ማለ​ዳም በተ​ነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድ​ኖች ሆነው አገ​ኙ​አ​ቸው።


ከን​ፈ​ራ​ቸ​ውም እንደ ተከ​ፈተ መቃ​ብር ነው፤ ሁሉም ኀያ​ላን ናቸው።


በሞት እቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ አን​ተ​ንና የአ​ባ​ት​ህን ቤት ግን ለታ​ላ​ቅና ከዚህ ለሚ​በዛ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” አለው።


እኒ​ህን ሕዝብ እንደ አንድ ሰው ብት​ገ​ድል ስም​ህን የሰሙ አሕ​ዛብ፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦


“ከዚህ ማኅ​በር መካ​ከል ፈቀቅ በሉ፥ እኔም በቅ​ጽ​በት አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።” በግ​ን​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደቁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ማጕ​ረ​ም​ረ​ማ​ቸው ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ጠፋ፥ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሞቱ ለማ​ይ​ሰሙ ልጆች ምል​ክት ሆና ትጠ​በቅ ዘንድ የአ​ሮ​ንን በትር በም​ስ​ክሩ ፊት አኑር።”


ሌላም ብዙ ነገር ነገ​ራ​ቸው፤ “ከዚህ ከክፉ ዓለ​ምም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ” ብሎ መከ​ራ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኀጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች