Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 10:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ባረ​ፈም ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ወደ እስ​ራ​ኤል እልፍ አእ​ላ​ፋት ተመ​ለስ” ይል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ታቦቱ ለጕዞ በተነሣ ጊዜ ሁሉ ሙሴ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ! ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ” ይል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 የቃል ኪዳኑ ታቦት በተንቀሳቀሰ ጊዜ ሁሉ ሙሴ “እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ሁሉ ከፊትህ ይባረሩ!” ይል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ ይል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 10:35
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ማዳን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ በረ​ከ​ት​ህም በሕ​ዝ​ብህ ላይ ነው።


አቤቱ፥ ተነሥ፥ ሰውም አይ​በ​ርታ፥ አሕ​ዛ​ብም በፊ​ትህ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸው።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ የክ​ን​ድ​ሽ​ንም ኀይል ልበሺ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ዘመን እንደ ጥንቱ ትው​ልድ ተነሺ።


ሰይ​ፌን እንደ መብ​ረቅ እስ​ላ​ታ​ለሁ፤ እጄም ፍር​ድን ትይ​ዛ​ለች፤ ለሚ​ጠ​ሉ​ኝም ፍዳ​ቸ​ውን እከ​ፍ​ላ​ለሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ንም እበ​ቀ​ላ​ለሁ።


የሚ​ጠ​ሉ​ትን ለማ​ጥ​ፋት በፊ​ታ​ቸው ብድ​ራት ይመ​ል​ስ​ባ​ቸ​ዋል፤ ለሚ​ጠ​ላው አይ​ዘ​ገ​ይም፤ ነገር ግን በፊቱ ብድ​ራ​ትን ይመ​ል​ስ​በ​ታል።


ሕዝ​ቡም ወደ ሰፈር በተ​መ​ለሱ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ስለ​ምን ጣለን? በፊ​ታ​ችን እን​ድ​ት​ሄድ፥ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ንም እጅ እን​ድ​ታ​ድ​ነን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከሴሎ እና​ምጣ” አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች