Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያ​ሱና የቀ​ድ​ም​ኤል ልጆች፥ የሰ​ራ​ብያ ልጅ ሴኬ​ንያ፥ የከ​ናኒ ልጆ​ችም በደ​ረ​ጃ​ዎች ላይ ቆመው ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በታ​ላቅ ድምፅ ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሌዋውያኑ ኢያሱ፣ ባኒ፣ ቀድምኤል፣ ሰበንያ፣ ቡኒ፣ ሰራብያ፣ ባኒ፣ ክናኒ፣ በመውጫ ደረጃዎች ላይ ቆሙ፤ ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔርም በታላቅ ድምፅ ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በሌዋውያኑ መድረክ ላይ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ቃድምኤል፥ ሽባንያ፥ ቡኒ፥ ሼሬብያ፥ ባኒ፥ ክናኒ ቆመው ወደ ጌታ አምላካቸው በታላቅ ድምፅ ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ለሌዋውያኑ መቆሚያ መድረክ ነበር፤ በዚያም ላይ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ቃድሚኤል፥ ሸባንያ፥ ቡኒ፥ ሼሬብያ፥ ባኒና ከናኒ በመቆም፥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሌዋውያኑም ኢያሱና ባኒ፥ ቀድምኤል፥ ሰበንያ፥ ቡኒ፥ ሰራብያ፥ ባኒ፥ ክናኒ በደረጃዎች ላይ ቆመው ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር በታላቅ ድምፅ ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 9:4
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሌዋ​ው​ያ​ንም፥ ከቀ​ዓት ልጆ​ችና ከቆሬ ልጆች የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከፍ ባለ ታላቅ ድምፅ ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ቆሙ።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያሱ፥ በንዊ፥ ቀድ​ም​ኤል፥ ሰራ​ብያ፥ ይሁዳ፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ጋር በመ​ዘ​ም​ራን ላይ የተ​ሾመ ማታ​ንያ።


ከእ​ር​ሱም በኋላ ሌዋ​ው​ያ​ንና የባኒ ልጅ ሬሁም ሠሩ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የቅ​ዒላ ግዛት እኩ​ሌ​ታና የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ችዋ ገዢ አሰ​ብያ ሠራ።


ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ ስለ​ዚህ ነገር በተ​ሠራ በዕ​ን​ጨት መረ​ባ​ርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ጠ​ገቡ መቲ​ትያ፥ ሰምያ፥ ሐና​ንያ፤ ኦርያ፥ ሕል​ቅያ፥ መዕ​ሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳ​ኤል፥ ሚል​ክያ፥ ሐሱም፥ ሐስ​በ​ዳና፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሜሱ​ላም በግ​ራው በኩል ቆመው ነበር።


ደግሞ ኢያ​ሱና ባኒ፥ ሰራ​ብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሳባ​ታይ፥ ሆዲያ፥ መዕ​ሤያ፥ ቆሊጣ፥ ዓዛ​ርያ፥ ኢዮ​ዛ​ባድ፥ ሐናን፥ ፌል​ዕያ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ሕጉን ለሕ​ዝቡ ያስ​ተ​ምሩ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ቆመው ነበር።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያ​ሱና ቀድ​ም​ኤል፥ እን​ዲህ አሉ፥ “ቆማ​ችሁ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ። የከ​በረ ስሙ​ንም አመ​ስ​ግኑ፤ በበ​ረ​ከ​ትና በም​ስ​ጋ​ናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድ​ር​ጉት።”


አቤቱ፥ ልቤ አይ​ታ​በ​ይ​ብ​ኝ፥ ዐይ​ኖ​ቼም ከፍ ከፍ አይ​በ​ሉ​ብኝ፤ ከት​ል​ል​ቆች ጋር፥ ከእ​ኔም ይልቅ ከሚ​ከ​ብሩ ጋር አል​ሄ​ድ​ሁም።


በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፤ ከተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራ​ውም ሰማኝ።


ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድ​ምጡ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁ​ንም ወደ አፌ ቃል አዘ​ን​ብሉ።


በጠ​ራ​ሁና በጮ​ኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ተከ​ለ​ከለ።


ይህ​ንም ብሎ በታ​ላቅ ቃል ጮኸና፥ “አል​ዓ​ዛር፥ ና፤ ወደ ውጭ ውጣ” አለ።


በጕ​ል​በ​ቱም ተን​በ​ር​ክኮ፥ “አቤቱ፥ ይህን ኀጢ​አት አት​ቍ​ጠ​ር​ባ​ቸው” ብሎ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህ​ንም ብሎ ሞተ፤ ሳው​ልም በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ ሞት ተባ​ባሪ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች