Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 8:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዕዝ​ራም የሕ​ዝቡ ሁሉ የበ​ላይ ነበ​ረና በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት መጽ​ሐ​ፉን ገለጠ፤ በገ​ለ​ጠ​ውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዕዝራም መጽሐፉን ከፈተ፤ ከሕዝቡ ከፍ ብሎ ቆሞ ስለ ነበረ፣ ሁሉም ያዩት ነበረ፣ በከፈተውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዕዝራም ከሕዝቡ ሁሉ በላይ ከፍ ብሎ ነበርና በሕዝቡ ሁሉ ዐይን ፊት መጽሐፉን ከፈተ፤ በከፈተውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ዕዝራ ከሕዝቡ ከፍ ብሎ በተሠራው መድረክ ላይ በቆመ ጊዜ፥ ሁሉም ትኲር ብለው ይመለከቱት ነበር፤ እርሱም የሕጉን መጽሐፍ በከፈተ ጊዜ፥ ሁሉም ከተቀመጡበት ተነሡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዕዝራም በሕዝቡ ሁሉ ላይ ከፍ ብሎ ሕዝቡ ሁሉ እያዩ መጽሐፉን ገለጠ በገለጠውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 8:5
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በደ​መ​ናው ውስጥ እኖ​ራ​ለሁ ብሎ​አል፤


ንጉ​ሡም ፊቱን ዘወር አድ​ርጎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጉባኤ ሁሉ መረ​ቃ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ ቆመው ነበር።


በው​ኃ​ውም በር ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ላይ ቆሞ፥ በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች በሚ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ትም ፊት፥ ከማ​ለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነ​በ​በው፤ የሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ጆሮ የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ለመ​ስ​ማት ያደ​ምጥ ነበር።


ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ ስለ​ዚህ ነገር በተ​ሠራ በዕ​ን​ጨት መረ​ባ​ርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ጠ​ገቡ መቲ​ትያ፥ ሰምያ፥ ሐና​ንያ፤ ኦርያ፥ ሕል​ቅያ፥ መዕ​ሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳ​ኤል፥ ሚል​ክያ፥ ሐሱም፥ ሐስ​በ​ዳና፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሜሱ​ላም በግ​ራው በኩል ቆመው ነበር።


ናዖ​ድም ወደ እርሱ ገባ፤ እር​ሱም በበጋ ቤቱ ሰገ​ነት ለብ​ቻው ተቀ​ምጦ ነበር። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክት ለአ​ንተ አለኝ” አለው። ዔግ​ሎ​ምም ከዙ​ፋኑ ተነሣ፥ ቀረ​በ​ውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች