ነህምያ 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 እነርሱም ሁሉ ሥራው እንዳይፈጸም፥ “እጃቸው ይደክማል” ብለው አስፈራሩን፤ ስለዚህም እጆችን አበረታሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ሁሉም፣ “እጃቸው መሥራት እስኪሳነው ድረስ ይዝላል፤ ሥራውም ሳይጠናቀቅ ይቀራል” ብለው በማሰብ ሊያስፈራሩን ሞከሩ። እኔ ግን፣ “አሁንም እጄን አበርታ” ስል ጸለይሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ሁሉም እንዲህ እያሉ አስፈራሩን፦ “ከሥራው እጃቸውን ያላላሉ፥ አይሠራምም” አሁንም እጄን አበርታ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 በዚህም ዐይነት ሥራውን እንድናቆም ለማድረግ ያስፈራሩን ነበር፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እባክህ አበርታኝ!” ስል ጸለይኩ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 እነርሱም ሁሉ ሥራው እንዳይፈጸም፦ እጃቸው ይደክማል ብለው ያስፈራሩን ዘንድ ወደዱ፥ አሁንም፥ አምላክ ሆይ፥ እጄን አበርታ። ምዕራፉን ተመልከት |