Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 6:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “አን​ተና አይ​ሁድ ዓመፃ እን​ድ​ታ​ስቡ፥ ስለ​ዚ​ህም ቅጥ​ሩን እን​ድ​ት​ሠራ፥ ንጉ​ሣ​ቸ​ውም ትሆን ዘንድ እን​ድ​ት​ወ​ድድ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ተሰ​ም​ቶ​አል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የተጻፈበትም እንዲህ የሚል ነበር፤ “አንተና አይሁዳውያን ለማመፅ እንደምትዶልቱና ቅጥሩንም እንደምትሠሩ በሕዝቦች መካከል ተወርቷል፤ ጌሳምም እውነት መሆኑን አረጋግጧል፤ ከዚህም በተጨማሪ በተወራው መሠረት አንተ ንጉሣቸው እንደምትሆን፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በውስጡ የተጻፈውም እንዲህ የሚል ነበር፦ “አንተና አይሁድ ልታምጹ እንዳቀዳችሁ፥ ለዚህም ቅጥሩን እንደሠራህ፥ ንጉሣቸውም ልትሆን እንደምትፈልግ በአሕዛብ ዘንድ ተሰምቶአል ጌሼምም ብሎታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “አንተና ወገኖችህ የሆኑት አይሁድ ዐመፅ ለማስነሣት ማቀዳችሁንና የቅጽር ግንቦችንም የምትሠሩት በዚሁ ምክንያት መሆኑን ጐረቤቶቻችን በሆኑ ሕዝቦች ዘንድ እንደሚወራ ጌሼም ነግሮኛል፤ ከዚህም ሌላ አንተ ራስህን ለማንገሥ ማሰብህንና፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በእጁም ውስጥ፦ አንተና አይሁድ ዓመፅ እንድታስቡ፥ ስለዚህም ቅጥሩን እንድትሠራ፥ ንጉሣቸውም ትሆን ዘንድ እንድትወድድ በአሕዛብ ዘንድ ተሰምቶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 6:6
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁ​ንም ከአ​ንተ ዘንድ የወጡ አይ​ሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ መጡ ጌታ​ቸው ንጉሡ ይወቅ፤ ዐመ​ፀ​ኛ​ዪ​ቱ​ንና እጅ​ግም የከ​ፋ​ች​ቱን ከተማ ይሠ​ራሉ፤ ቅጥ​ር​ዋ​ንም ያድ​ሳሉ፤ መሠ​ረ​ቷ​ንም ጠገኑ።


በአ​ባ​ቶ​ችህ ታሪክ መጽ​ሐፍ ምር​መራ ይደ​ረግ፤ በዚ​ያም በታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ይህች ከተማ ዐመ​ፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገ​ሥ​ታ​ት​ንና አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም እንደ ጎዳች፥ ከጥ​ን​ቱም የገ​ባ​ሮች ሽፍ​ት​ነት በእ​ር​ስዋ እንደ ተጀ​መረ ታገ​ኛ​ለህ፤ ታው​ቃ​ለ​ህም፤ ስለ​ዚ​ህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።


ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላጥ፥ አገ​ል​ጋ​ዩም አሞ​ና​ዊው ጦቢያ፥ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በን​ቀት ሳቁ​ብን፤ ቀላል አድ​ር​ገ​ው​ንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር ምን​ድን ነው? በውኑ በን​ጉሡ ላይ ትሸ​ፍቱ ዘንድ ትወ​ድ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” አሉ።


ይህ​ንም ነገር አደ​ር​ግና እበ​ድል ዘንድ፥ በእ​ኔም ላይ ክፋት እን​ዲ​ና​ገ​ሩና እን​ዲ​ያ​ላ​ግጡ ያስ​ፈ​ራ​ራኝ ዘንድ ተገ​ዝቶ ነበር።


ሰን​ባ​ላ​ጥም እንደ ፊተ​ኛው ብላ​ቴ​ና​ውን አም​ስ​ተኛ ጊዜ ላከ​ብኝ፤ በእ​ጁም ውስጥ እን​ዲህ የሚል ግልጥ ደብ​ዳቤ ነበረ፦


ደግ​ሞም፦ ንጉሥ በይ​ሁዳ አለ ብለው ስለ አንተ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይና​ገሩ ዘንድ ነቢ​ያ​ትን አቁ​መ​ሃል፤ አሁ​ንም ለን​ጉሡ ይህን ቃል ያወ​ሩ​ለ​ታል፤ እን​ግ​ዲህ መጥ​ተህ በአ​ን​ድ​ነት እን​ማ​ከር።”


በእኔ ላይ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና የከ​በ​ቡ​ኝን የብዙ ሰዎ​ችን ስድብ ሰም​ቻ​ለሁ፤ መው​ደ​ቄን የሚ​ጠ​ብቁ የሰ​ላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምና​ል​ባት ይታ​ለል እንደ ሆነ፥ እና​ሸ​ን​ፈ​ውም እንደ ሆነ፥ እር​ሱ​ንም እን​በ​ቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እን​ነ​ሣ​ለን” ይላሉ።


“ቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።


እን​ዲ​ህም እያሉ ይከ​ስ​ሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄ​ሣር ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሲከ​ለ​ክ​ልና ሕዝ​ቡን ሲያ​ሳ​ምፅ፥ ራሱ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ክር​ስ​ቶ​ስን ሲያ​ደ​ርግ አገ​ኘ​ነው።”


ጲላ​ጦ​ስም ይህን ሰምቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ወደ ውጭ አወ​ጣው፤ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥም ገበታ ተብሎ በሚ​ጠ​ራው “ጸፍ​ጸፍ” በሚ​ሉት ቦታ ላይ በወ​ን​በር ተቀ​መጠ።


በውኑ እና መል​ካም ነገር እና​ገኝ ዘንድ ክፉ ነገር እና​ድ​ርግ እን​ደ​ም​ንል አስ​መ​ስ​ለው የሚ​ጠ​ረ​ጥ​ሩ​ንና የሚ​ነ​ቅ​ፉን ሰዎች እን​ደ​ሚ​ሰ​ድ​ቡን ነን? ለእ​ነ​ር​ሱስ ቅጣ​ታ​ቸው ተዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላ​ቸ​ዋል።


በክ​ብ​ርና በው​ር​ደት፥ በም​ር​ቃ​ትና በር​ግ​ማን፥ እንደ አሳ​ቾች ስን​ታይ እው​ነ​ተ​ኞች ነን።


በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች