Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የቤ​ት​ሐ​ካ​ሪ​ምም ግዛት ገዢ የሬ​ካብ ልጅ መል​ክያ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹና ከል​ጆቹ ጋር የጕ​ድፍ መጣ​ያ​ውን በር ሠራ፤ ከደ​ነው፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የቈሻሻ መጣያ በር ተብሎ የሚጠራው የቤትሐካሪም አውራጃ ገዥ የሆነው የሬካብ ልጅ መልክያ መልሶ ሠራ፤ መልሶ ከሠራ በኋላም መዝጊያዎቹን፣ መቀርቀሪያዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የቤትሐካሪም አውራጃ ገዢ የሬካብ ልጅ ማልኪያ “የፍግ በር” አደሰ፤ መልሶ ሠራው፥ በሮቹን አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የቤትሀካሬም ወረዳ ገዢ የሆነው የሬካብ ልጅ ማልኪያ የጒድፍ መጣያውን ቅጽር በር በማደስ ሠራ፤ በሮችን ገጠመ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የቤትሐካሪምም ግዛት አለቃ የሬካብ ልጅ መልክያ የጉድፍ መጣያውን በር አደሰ፥ ሠራው፥ ሳንቃዎቹንም አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 3:14
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለኢ​ያ​ቡ​ስቴ የጭ​ፍራ አለ​ቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ደ​ኛው ስም በዓና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሬካብ ነበረ፤ ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች የቤ​ሮ​ታ​ዊው የሬ​ሞን ልጆች ነበሩ፤ ቤሮ​ትም ለብ​ን​ያም ተቈ​ጥራ ነበር።


ከዚ​ያም በሄደ ጊዜ የሬ​ካ​ብን ልጅ ኢዮ​ና​ዳ​ብን በመ​ን​ገድ አገ​ኘው፤ ተቀ​ብ​ሎም መረ​ቀው፤ ኢዩም፥ “ልቤ ከል​ብህ ጋር ቅን እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅ​ን​ነት ነውን?” አለው። ኢዮ​ና​ዳ​ብም፥ “አዎን” አለው። ኢዩም፥ “እው​ነ​ት​ህስ ከሆነ እጅ​ህን ስጠኝ” አለ። እጁ​ንም ሰጠው፤ ወደ እር​ሱም ወደ ሰረ​ገ​ላው አወ​ጣው።


የሚ​ካ​ኤል ልጅ፤ የበ​ዓ​ሣያ ልጅ፥ የመ​ል​ክያ ልጅ፤


የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች ወደ ቅጥሩ አወ​ጣ​ኋ​ቸው፤ አመ​ስ​ጋ​ኞ​ቹ​ንም በሁ​ለት ታላ​ላቅ ተርታ አቆ​ም​ኋ​ቸው፤ የአ​ን​ዱም ተርታ ሰዎች ወደ ቀኝ በቅ​ጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣ​ያው በር ሄዱ።


በሸ​ለ​ቆ​ውም በር ወጣሁ፤ ወደ በለ​ስም ምን​ጭና ወደ ጕድፍ መጣ​ያው በር ሄድሁ፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር፥ በእ​ሳ​ትም የተ​ቃ​ጠ​ሉ​ትን በሮ​ች​ዋን ተመ​ለ​ከ​ትሁ።


በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ግዛት እኩ​ሌታ አለቃ የሆር ልጅ ረፋያ ሠራ።


እና​ንተ የብ​ን​ያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላ​ቅም ጥፋት ከመ​ስዕ ይጐ​በ​ኛ​ልና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ለመ​ሸሽ ጽኑ፤ በቴ​ቁሔ መለ​ከ​ቱን ንፉ፤ በቤ​ት​ካ​ሪም ላይ ምል​ክ​ትን አንሡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች