Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 2:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ንግ​ሥ​ቲ​ቱም፦ በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​ምጣ ሳለች ንጉሡ፥ “መን​ገ​ድህ እስከ መቼ ድረስ ይሆ​ናል? መቼስ ትመ​ለ​ሳ​ለህ?” አለኝ። ንጉ​ሡም ይሰ​ድ​ደኝ ዘንድ ደስ አለው፤ እኔም ጊዜ​ውን ነገ​ር​ሁት፤ እር​ሱም አሰ​ና​በ​ተኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከዚያም ንጉሡ አጠገቡ ከተቀመጠችው ንግሥት ጋራ በመሆን፣ “ጕዞህ ምን ያህል ቀን ይፈጃል? መቼስ ትመለሳለህ?” ሲል ጠየቀኝ። ንጉሡም እኔን ለመስደድ ደስ አለው፤ እኔም ጊዜውን ወሰንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ንግሥቲቱ በአጠገቡ ተቀምጣ ሳለች ንጉሡ፦ “መንገድህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል? መቼስ ትመለሳለህ?” አለኝ። ንጉሡም ሊልከኝ ወደደ፤ እኔም ጊዜውን ወሰኜ ነገርኩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በዚህን ጊዜ ንግሥቲቱ በንጉሠ ነገሥቱ አጠገብ ተቀምጣ ነበር፤ ንጉሠ ነገሥቱም ጥያቄዬን በመቀበል፦ “ጒዞህ ምን ያኽል ጊዜ ይወስድብሃል? እስከ መቼስ ትመለሳለህ?” ብሎ ጠየቀኝ። እኔም የሚወስድብኝን ጊዜና መቼ እንደምመለስ ነገርኩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ንግሥቲቱም በአጠገቡ ተቀምጣ ሳለች ንጉሡ፦ “መንገድህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል? መቼስ ትመለሳለህ?” አለኝ። ንጉሡም ይሰድደኝ ዘንድ ደስ አለው፤ እኔም ዘመኑን ቀጠርሁለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 2:6
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባ​ሪ​ያ​ህን ጸሎት፥ ስም​ህ​ንም ይፈሩ ዘንድ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ትን የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ጸሎት ያድ​ምጥ፤ ዛሬም ለባ​ሪ​ያህ አከ​ና​ው​ን​ለት፤ በዚ​ህም ሰው ፊት ምሕ​ረ​ትን ስጠው።” እኔም ለን​ጉሡ ጠጅ አሳ​ላፊ ነበ​ርሁ።


እኔ ግን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሠ​ላሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበ​ርና በዚህ ጊዜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ነ​በ​ር​ሁም። ከጥ​ቂት ዘመ​ንም በኋላ የን​ጉ​ሡን ፈቃድ ለመ​ንሁ፤


ንጉ​ሡም፥ “ምን ትለ​ም​ነ​ኛ​ለህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አም​ላክ ጸለ​ይሁ።


ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉ​ሡን ደስ ቢያ​ሰ​ኝህ፥ ባሪ​ያ​ህም በፊ​ትህ ሞገስ ቢያ​ገኝ፥ እሠ​ራው ዘንድ ወደ ይሁዳ ወደ አባ​ቶች መቃ​ብር ከተማ ስደ​ደኝ” አል​ሁት።


ንጉ​ሡም በይ​ሁዳ ምድር ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ካዘ​ዘኝ ጊዜ ጀምሮ ከን​ጉሡ ከአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ከሃ​ያ​ኛው ዓመት እስከ ሠላሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል እኔና ወን​ድ​ሞች ለአ​ለቃ የሚ​ገ​ባ​ውን ቀለብ አል​በ​ላ​ንም።


ከድሮ ዘመን የፈ​ረ​ሱት ስፍ​ራ​ዎ​ችህ ይሠ​ራሉ፤ መሠ​ረ​ት​ህም ለልጅ ልጅ ዘመን ይሆ​ናል፤ አን​ተም፦ ሰባ​ራ​ውን ጠጋኝ፥ የመ​ኖ​ሪያ መን​ገ​ድ​ንም አዳሽ ትባ​ላ​ለህ።


ከጥ​ንት ጀምሮ የፈ​ረ​ሱ​ትን ይሠ​ራሉ፤ ከቀ​ድሞ ጀምሮ የፈ​ረ​ሱ​ት​ንም ያቆ​ማሉ፤ ባድማ የነ​በ​ሩ​ት​ንና ከብዙ ትው​ልድ በፊት የፈ​ረ​ሱ​ትን ከተ​ሞች እንደ ገና ያድ​ሳሉ።


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ሳይ​ጠሩ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ገናም ሲና​ገሩ እነሆ፥ አለሁ እላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች