Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 2:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የአ​ም​ላ​ኬም እጅ በእኔ ላይ መል​ካም እንደ ሆነች፥ ንጉ​ሡም የነ​ገ​ረ​ኝን ቃል ነገ​ር​ኋ​ቸው። “ተነሡ እን​ሥራ” አል​ኋ​ቸው። እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለበጎ ሥራ አበ​ረቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንዲሁም መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ እንደ ነበረችና ንጉሡም ምን እንዳለኝ ነገርኋቸው። እነርሱም፣ “እንደ ገና መሥራቱን እንጀምር!” ካሉ በኋላ ይህን መልካም ሥራ ጀመሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 መልካም የሆነችው የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ እንደሆነችና ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ “እንነሣና እንሥራ” አሉ። ለመልካም ሥራ እጃቸውን አበረቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ቀጠል አድርጌም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑንና እንዴትም እንደ ረዳኝ፥ ንጉሠ ነገሥቱም የነገረኝን ሁሉ ገለጥሁላቸው። እነርሱም “እንደገና መሥራቱን እንጀምር!” ካሉኝ በኋላ፥ ይህን በጎ ሥራ ለመጀመር ተዘጋጁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ “እንነሣና እንሥራ” አሉ። እጃቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 2:18
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁ​ንም ጌታ​ችሁ ሳኦል ሞቶ​አ​ልና እጃ​ችሁ ትጽና፤ እና​ን​ተም በርቱ፤ የይ​ሁ​ዳም ቤት በእ​ነ​ርሱ ላይ ንጉሥ እሆን ዘንድ ቀብ​ተ​ው​ኛል።”


ለዳ​ዊ​ትም የነ​በ​ሩት ኀያ​ላን አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ስለ እስ​ራ​ኤል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ጋር በመ​ን​ግ​ሥቱ አጸ​ኑት።


አይ​ዞህ፥ በርታ፤ ስለ ሕዝ​ባ​ች​ንና ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ከተ​ሞች እን​በ​ርታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቱ ደስ ያሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ” አለ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ሰው​ነ​ቱን አጽ​ናና፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላ​ዩም ግንብ ሠራ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በስ​ተ​ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊ​ትም ከተማ የሚ​ያ​ወ​ጣ​ውን በር አጠ​ነ​ከረ፤ ብዙም መሣ​ሪ​ያና ጋሻ አዘ​ጋጀ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት እጃ​ቸ​ውን ያጸና ዘንድ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ልብ ወደ እነ​ርሱ መል​ሶ​አ​ልና የቂ​ጣ​ውን በዓል ሰባት ቀን በደ​ስታ አደ​ረጉ።


በቤ​ቱም አጠ​ገብ ላለው ለግ​ንብ በሮች፥ ለከ​ተ​ማ​ውም ቅጥር፥ ለም​ገ​ባ​በ​ትም ቤት እን​ጨት እን​ዲ​ሰ​ጠኝ ለን​ጉሡ ዱር ጠባቂ ለአ​ሳፍ ደብ​ዳቤ ይሰ​ጠኝ” አል​ሁት። ንጉ​ሡም ሁሉን ሰጠኝ። የከ​በ​ረች የአ​ም​ላኬ እጅ ከእኔ ጋር ነበ​ረ​ችና።


እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በኀ​ይሉ ጽናት በርቱ።


ለሚ​ወ​ደው ሥራ የሚ​ረ​ዳ​ችሁ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታ​ውን ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ።


የሳ​ኦ​ልም ልጅ ዮና​ታን ተነ​ሥቶ ወደ ዳዊት ወደ ቄኒ ሄደ። እጁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጸና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች