Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 13:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለሌ​ዋ​ው​ያን፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ንና ለበ​ረ​ኞቹ እንደ ሕጉ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና ዕጣ​ኑን፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም፥ የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንም ዐሥ​ራት፥ ለካ​ህ​ና​ቱም የሆ​ነ​ውን ቀዳ​ም​ያ​ቱን አስ​ቀ​ድሞ ያስ​ቀ​መ​ጡ​በ​ትን ታላቅ ዕቃ ቤት አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ለት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከዚህ በፊት የእህል ቍርባኑ፣ ዕጣኑ፣ የቤተ መቅደሱ ዕቃዎች፣ የእህሉ ዐሥራትና፣ ለሌዋውያን፣ ለመዘምራንና ለበር ጠባቂዎች የታዘዘው አዲሱ ወይንና ዘይት፣ ለካህናቱም የሚመጣው ስጦታ ይቀመጥበት የነበረውን ትልቁን የዕቃ ቤት እንዲኖርበት ሰጥቶት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ትልቅ ለሌዋውያን፥ ለመዘምራን፥ ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን የእህሉን ቁርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት፥ ለካህናቱም የሆነውን የማንሣት ቁርባን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቁን ጓዳ አዘጋጅቶለት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚህም የተነሣ የእህል መባ፥ ዕጣን፥ የቤተ መቅደስ ንዋያተ ቅድሳት፥ ከእህል፥ ከወይን ጠጅ፥ ከወይራ ዘይት ተውጣጥቶ ለሌዋውያኑ ለቤተ መቅደስ መዘምራንና ለዘብ ጠባቂዎች የሚሰጠው ዐሥራትና ለካህናቱ የሚሰጥ መባ ሁሉ እንዲቀመጥበት ታስቦ በተለይ የተሠራውን ታላቅ ክፍል ጦቢያ በመኖሪያነት ይጠቀምበት ዘንድ ኤልያሺብ ፈቅዶለት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ለሌዋውያን፥ ለመዘምራን፥ ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን የእህሉን ቁርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት፥ ለካህናቱም የሆነውን የማንሣት ቁርባን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቁን ጓዳ አዘጋጅቶለት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 13:5
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጎተራ ያዘ​ጋጁ ዘንድ አዘዘ፤ እነ​ር​ሱም አዘ​ጋጁ።


የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ላፈ​ረ​ሱት ቤት ሰረ​ገ​ሎች ያደ​ርጉ ዘንድ፥ ለማ​ጋ​ጠ​ሚ​ያም እን​ጨት፥ የተ​ጠ​ረ​በ​ው​ንም ድን​ጋይ ይገዙ ዘንድ ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችና ለጠ​ራ​ቢ​ዎች ሰጡ።


በሕ​ጉም እንደ ተጻፈ የል​ጆ​ቻ​ች​ን​ንና የእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ንን በኵ​ራት፥ የበ​ሬ​ዎ​ቻ​ች​ን​ንና የበ​ጎ​ቻ​ች​ንን በኵ​ራት በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት ወደ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ካህ​ናት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት እና​መጣ ዘንድ፥


የእ​ህ​ላ​ች​ን​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ የዛ​ፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወ​ይ​ኑ​ንና የዘ​ይ​ቱ​ንም ፍሬ ወደ ካህ​ናቱ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ጓዳ​ዎች እና​መጣ ዘንድ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን እርሻ ሁሉ ዐሥ​ራት ይቀ​በ​ላ​ሉና የመ​ሬ​ታ​ች​ንን ዐሥ​ራት ወደ ሌዋ​ው​ያን እና​መጣ ዘንድ ማልን።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም ዐሥ​ራ​ቱን በተ​ቀ​በሉ ጊዜ የአ​ሮን ልጅ ካህኑ ከሌ​ዋ​ው​ያን ጋር ይሁን፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም የዐ​ሥ​ራ​ቱን ዐሥ​ራት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ወደ ጓዳ​ዎች ወደ ዕቃ ቤት ያም​ጡት።


የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ደስ ስላ​ላ​ቸው፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከ​ተ​ሞች እር​ሻ​ዎች ያከ​ማቹ ዘንድ ለቀ​ዳ​ም​ያት፥ ለዐ​ሥ​ራ​ትም በየ​ዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎ​ችን ሾሙ።


ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጣሁ፤ ኤል​ያ​ሴ​ብም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ለጦ​ቢያ ዕቃ ቤቱን በማ​ዘ​ጋ​ጀት ያደ​ረ​ገ​ውን ክፉ ነገር አስ​ተ​ዋ​ልሁ።


በበ​ሮ​ቹም በግ​ንቡ አዕ​ማድ አጠ​ገብ ዕቃ ቤቱና መዝ​ጊ​ያው ነበሩ፤ በዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያጥቡ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች