Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 26:69 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

69 ጴጥሮስም ከቤት ውጭ በአጥሩ ግቢ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድም ወደ እርሱ ቀርባ “አንተ ደግሞ ከገሊላው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ፤” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

69 ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ ሳለ አንዲት የቤት ሠራተኛ ወደ እርሱ ቀርባ፣ “አንተም ከገሊላው ኢየሱስ ጋራ ነበርህ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

69 ጴጥሮስም ከቤት ውጪ በግቢው ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድ ወደ እርሱ ቀርባ “አንተም ከገሊላዊው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

69 ጴጥሮስ ከቤት ውጪ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ በዚያን ጊዜ አንዲት ገረድ ወደ እርሱ ቀርባ “አንተም ከገሊላዊው ኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

69 ጴጥሮስም ከቤት ውጭ በአጥሩ ግቢ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድም ወደ እርሱ ቀርባ፦ አንተ ደግሞ ከገሊላው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 26:69
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤል​ያ​ስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊ​ያው ሸፈነ፤ ወጥ​ቶም በዋ​ሻው ደጃፍ ቆመ። እነ​ሆም፥ “ኤል​ያስ ሆይ፥ ወደ​ዚህ ለምን መጣህ?” የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ።


እዚ​ያም ወዳለ ዋሻ ገባ፤ በዚ​ያም አደረ፤ እነ​ሆም፥ “ኤል​ያስ ሆይ! ምን አመ​ጣህ?” የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።


ምስ​ጉን ነው፥ በዝ​ን​ጉ​ዎች ምክር ያል​ሄደ፥ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም መን​ገድ ያል​ቆመ፥ በዋ​ዘ​ኞ​ችም ወን​በር ያል​ተ​ቀ​መጠ ሰው።


ሕዝቡም “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው፤” አሉ።


በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፤


ጴጥሮስ ግን እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፤ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ።


እርሱ ግን “የምትዪውን አላውቀውም፤” ብሎ በሁሉ ፊት ካደ።


ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት “ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ፤” አለች።


ፊል​ጶ​ስም ናት​ና​ኤ​ልን አገ​ኘ​ውና፥ “ሙሴ በኦ​ሪት፥ ነቢ​ያ​ትም ስለ እርሱ የጻ​ፉ​ለ​ትን የዮ​ሴ​ፍን ልጅ የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን አገ​ኘ​ነው” አለው።


“ክር​ስ​ቶስ ነው” ያሉም አሉ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም እን​ዲህ አሉ፥ “በውኑ ክር​ስ​ቶስ ከገ​ሊላ ይወ​ጣ​ልን?


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “አን​ተም ደግሞ ከገ​ሊላ ነህን? ከገ​ሊላ ነቢይ እን​ደ​ማ​ይ​ነሣ መር​ም​ርና እይ” አሉት።


ከእ​ር​ሱም በኋላ ሰዎች ለግ​ብር በተ​ቈ​ጠ​ሩ​በት ወራት ገሊ​ላ​ዊው ይሁዳ ተነሣ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ተከ​ተ​ሉት፤ እር​ሱም ሞተ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​ትም ሁሉ ተበ​ታ​ተኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች