Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 26:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ስለ ብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ስለ ብዙዎች የኀጢአት ይቅርታ የሚፈስስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የኪዳን ደሜ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ይህ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 26:28
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እነሆ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ከይ​ሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የም​ገ​ባ​በት ወራት ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


የሥጋ ሁሉ ሕይ​ወት ደሙ ነው፤ ደሙም ከሕ​ይ​ወቱ የተ​ነሣ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ማስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእ​ና​ንተ ሰጠ​ሁት።


ለአንቺም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስሮችሽን ውኃ ከሌለበት ጕድጓድ አውጥቻለሁ።


እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”


ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው፤ እንዲህም አለ፤ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤


ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር ከዚህ ከወይን ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣም።”


እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤


ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኀጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።


እርሱም “ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።


ኅብ​ስ​ቱ​ንም አነሣ፤ አመ​ስ​ገነ፤ ፈት​ቶም ሰጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ስለ እና​ንተ ቤዛ ሆኖ የሚ​ሰጥ ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህ​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢ​ያዬ አድ​ር​ጉት፤”


እን​ዲ​ሁም ከእ​ራት በኋላ ጽዋ​ዉን አን​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ጽዋ ስለ እና​ንተ በሚ​ፈ​ስ​ሰው ደሜ የሚ​ሆን አዲስ ኪዳን ነው።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋው በበ​ደ​ላ​ችን መጠን የሆ​ነ​ብን አይ​ደ​ለም፤ በአ​ንድ ሰው በደል ብዙ​ዎች ከሞቱ፥ እን​ግ​ዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ፥ በአ​ንዱ ሰው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቤዛ​ነት በሰ​ጠን ሀብቱ ሕይ​ወት በብ​ዙ​ዎች ላይ እን​ዴት እጅግ ይበዛ ይሆን?


በአ​ንድ ሰው አለ​መ​ታ​ዘዝ ብዙ​ዎች ኀጢ​አ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ፥ እን​ዲሁ ደግሞ በአ​ንድ ሰው መታ​ዘዝ ብዙ​ዎች ጻድ​ቃን ይሆ​ናሉ።


እን​ዲ​ሁም ኅብ​ስ​ቱን ከተ​ቀ​በሉ በኋላ ጽዋ​ውን አን​ሥቶ፥ “አዲስ ሥር​ዐት የሚ​ጸ​ና​በት ይህ ጽዋ ደሜ ነው እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በም​ት​ጠ​ጡ​በ​ትም ጊዜ አስ​ቡኝ” አላ​ቸው።


በእ​ር​ሱም እንደ ቸር​ነቱ ብዛት በደሙ ድኅ​ነ​ትን አገ​ኘን፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም ተሰ​ረ​የ​ልን።


ድኅ​ነ​ትን ያገ​ኘ​ን​በት፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም የተ​ሠ​ረ​የ​በት ነው።


ሁሉ​ንም በእ​ርሱ ይቅር ይለው ዘንድ በመ​ስ​ቀሉ ባፈ​ሰ​ሰው ደም በም​ድ​ርና በሰ​ማ​ያት ላሉ ሰላ​ምን አደ​ረገ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ የከዳ፥ ያን​ንም የተ​ቀ​ደ​ሰ​በ​ትን የኪ​ዳ​ኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቈ​ጠረ፥ የጸ​ጋ​ው​ንም መን​ፈስ ያክ​ፋፋ እን​ዴት ይልቅ የሚ​ብስ ቅጣት የሚ​ገ​ባው ይመ​ስ​ላ​ች​ኋል?


በዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን ደም ለበ​ጎች ትልቅ እረኛ የሆ​ነ​ውን ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው፥


እን​ዲሁ ክር​ስ​ቶ​ስም የብ​ዙ​ዎ​ችን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ር​ጉት ያለ ኀጢ​አት ይገ​ለ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል።


እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።


እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። አለኝም “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።


ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች