Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 14:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው “ቦታው ምድረ በዳ ነው፤ አሁንም ሰዓቱ አልፎአል፤ ወደ መንደሮች ሄደው ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብት፤” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሊመሽ ሲል ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፣ “ይህ ስፍራ ምንም የማይገኝበት ምድረ በዳ ነው፤ ጊዜው እየመሸ ስለ ሆነ፣ ወደ መንደሮች ሄደው የሚበሉት ምግብ እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብት” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በመሸም ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው “ቦታው ምድረ በዳ ነው፤ ሰዓቱም አልፎአል፤ ወደ መንደሮች ሄደው ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብታቸው” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፥ “ይህ ቦታ ምድረ በዳ ነው፤ ቀኑም መሽቶአል፤ ስለዚህ ሕዝቡ በአቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች ሄደው ምግባቸውን እንዲገዙ አሰናብታቸው” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፦ ቦታው ምድረ በዳ ነው አሁንም ሰዓቱ አልፎአል፤ ወደ መንደሮች ሄደው ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብት አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 14:15
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስም በሰማ ጊዜ ከዚያ ብቻውን ወደ ምድረ በዳ በታንኳ ፈቀቅ አለ፤ ሕዝቡም ሰምተው ከከተማዎቹ በእግር ተከተሉት።


ወጥቶም ብዙ ሕዝብ አየና አዘነላቸው፤ ድውዮቻቸውንም ፈወሰ።


ኢየሱስም “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው እንጂ ሊሄዱ አያስፈልግም፤” አላቸው።


እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት፤” እያሉ ለመኑት።


ከእነርሱም አንዳንዶቹ ከሩቅ መጥተዋልና፥ ጦማቸውን ወደ ቤታቸው ባሰናብታቸው በመንገድ ይዝላሉ፤” አላቸው።


ቀኑም በመሸ ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት መጥ​ተው፥ “ያለ​ን​በት ምድረ በዳ ነውና በዙ​ሪ​ያ​ችን ወዳሉ መን​ደ​ሮ​ችና ገጠ​ሮች ሄደው እን​ዲ​ያ​ድሩ የሚ​በ​ሉ​ት​ንም እን​ዲ​ያ​ገኙ ሕዝ​ቡን አሰ​ና​ብት” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች