Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ደቀ መዛሙርቱም “በዚህ በምድረ በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል?” ብለው መለሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ደቀ መዛሙርቱም መልሰው፣ “በዚህ ምድረ በዳ እነዚህን ለመመገብ የሚያስችል እንጀራ ከወዴት ይገኛል?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ደቀ መዛሙርቱም መልሰው፥ “በዚህ ምድረ በዳ እነዚህን ለመመገብ የሚያስችል እንጀራ ከወዴት ይገኛል?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ደቀ መዛሙርቱም፦ “ታዲያ፥ በዚህ በረሓ ለእነዚህ ሁሉ ሰዎች የሚበቃ እንጀራ ማግኘት ማን ይችላል?” ሲሉ መለሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ደቀ መዛሙርቱም፦ በዚህ በምድረ በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል? ብለው መለሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 8:4
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም በእጁ ተደ​ግ​ፎት የሚ​ቆም የነ​በረ ያ ብላ​ቴና ለኤ​ል​ሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ የእ​ህል ሿሿቴ ቢያ​ደ​ርግ ይህ ነገር ይሆ​ና​ልን?” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “እነሆ፥ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ታየ​ዋ​ለህ፤ ከዚያ ግን አት​ቀ​ም​ስም” አለ።


ደቀ መዛሙርቱም “ይህን ያህል ሕዝብ የሚያጠግብ ይህን ያህል እንጀራ በምድረ በዳ ከወዴት እናገኛለን?” አሉት።


ስለ እንጀራው አላስተዋሉምና፤ ነገር ግን ልባቸው ደንዝዞ ነበር።


ከእነርሱም አንዳንዶቹ ከሩቅ መጥተዋልና፥ ጦማቸውን ወደ ቤታቸው ባሰናብታቸው በመንገድ ይዝላሉ፤” አላቸው።


እርሱም “ስንት እንጀራ አላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው፤ እነርሱም “ሰባት” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች