Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 8:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከዚህም በኋላ ደግሞ እጁን በዐይኑ ላይ ጫነበት፤ አጥርቶም አየ፤ ዳነም፤ ከሩቅም ሳይቀር ሁሉን ተመለከተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ኢየሱስም እንደ ገና እጆቹን በሰውየው ዐይኖች ላይ ጫነ፤ በዚህ ጊዜ ዐይኖቹ በሩ፤ ብርሃኑም ተመለሰለት፤ ሁሉንም ነገር አጥርቶ ማየት ቻለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ኢየሱስም እንደገና እጆቹን በሰውየው ዐይኖች ላይ ጫነ፤ በዚህ ጊዜ ዐይኖቹ በሩ፤ ብርሃኑም ተመለሰለት፤ ሁሉንም ነገር አጥርቶ ማየት ቻለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እንደገናም ኢየሱስ በሰውየው ዐይኖች ላይ እጁን ጫነ፤ በዚህ ጊዜ ሰውየው ትኲር ብሎ አየ፤ ድኖም ሁሉን ነገር አጥርቶ ማየት ጀመረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ከዚህም በኋላ ደግሞ እጁን በዓይኑ ላይ ጫነበት አጥርቶም አየና ዳነም ከሩቅም ሳይቀር ሁሉን ተመለከተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 8:25
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጻድቃን መንገዶች ግን እንደ ብርሃን ይበራሉ። ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየጨመሩ ይበራሉ።


ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።


አሻቅቦም “ሰዎች እንደ ዛፍ ሲመላለሱ አያለሁ፤” አለ።


ወደ ቤቱም ሰደደውና “ወደ መንደሩ አትግባ፤ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር፤” አለው።


እነ​ር​ሱም ወደ ሰማይ አተ​ኵ​ረው ሲመ​ለ​ከቱ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች ነጫጭ ልብስ ለብ​ሰው በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ቆመው ታዩ​አ​ቸው።


እር​ሱም ጳው​ሎ​ስን ሲያ​ስ​ተ​ምር ሰማው፤ ጳው​ሎ​ስም ትኩር ብሎ ተመ​ለ​ከ​ተው፤ እም​ነት እን​ዳ​ለ​ውና እን​ደ​ሚ​ድ​ንም ተረዳ።


እርሱ የጀ​መ​ረ​ላ​ች​ሁን በጎ​ውን ሥራ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እስ​ከ​ሚ​መ​ጣ​በት ቀን ድረስ እርሱ እን​ደ​ሚ​ፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ አም​ና​ለሁ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች