Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 6:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ስሙም ተገልጦአልና ንጉሡ ሄሮድስ በሰማ ጊዜ “መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል፤ ስለዚህም ኀይል በእርሱ ይደረጋል፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የኢየሱስ ስም እየታወቀ በመምጣቱ፣ ንጉሥ ሄሮድስ ይህንኑ ሰማ። አንዳንዶችም፣ “የዚህ ዐይነት ታምር በርሱ የሚሠራው መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ቢነሣ ነው” ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የኢየሱስ ስም እየታወቀ በመምጣቱ፥ ንጉሥ ሄሮድስ ይህንኑ ሰማ። አንዳንዶችም፥ “የዚህ ዓይነት ታምር በእርሱ የሚሠራው መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ቢነሣ ነው” ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የኢየሱስ ዝና በሁሉም ዘንድ ስለ ታወቀ፥ ንጉሡ ሄሮድስ ስለ እርሱ ሰማ። አንዳንድ ሰዎች፥ “መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶአል፤ ስለዚህ ይህ ሁሉ ተአምራት በእርሱ ይደረጋል” ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ስሙም ተገልጦአልና ንጉሡ ሄሮድስ በሰማ ጊዜ፦ መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 6:14
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በብ​ል​ሃ​ተ​ኞች እጅ የተ​ሠ​ሩ​ትን ፥ በግ​ን​ብና በቅ​ጥር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን፥ ፍላ​ጻና መርግ የሚ​ወ​ረ​ወ​ር​ባ​ቸ​ውን መሣ​ሪ​ያ​ዎች አደ​ረገ፤ እስ​ኪ​በ​ረ​ታም ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በድ​ንቅ ረድ​ቶ​ታ​ልና የመ​ሣ​ሪ​ያ​ዎቹ ዝና እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ።


አሞ​ና​ው​ያ​ንም ለዖ​ዝ​ያን ገበሩ፤ እጅ​ግም በር​ትቶ ነበ​ርና ዝናው እስከ ግብፅ መግ​ቢያ ድረስ ተሰማ።


እነርሱ ግን ወጥተው በዚያ አገር ሁሉ ስለ እርሱ አወሩ።


ዝናውም ወዲያው በየስፍራው ወደ ገሊላ ዙሪያ ሁሉ ወጣ።


እርሱ ግን ሲወጣ ብዙ ሊሰብክና ነገሩን ሊያወራ ጀመረ፤ ስለዚህም ኢየሱስ ተገልጦ ወደ ከተማ መግባት ወደ ፊት ተሳነው፤ ነገር ግን በውጭ በምድረ በዳ ይኖር ነበር፤ ከየስፍራውም ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።


እነርሱም “መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ከነቢያት አንዱ” ብለው ነገሩት።


በዚ​ያ​ችም ቀን ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን ሰዎች መጥ​ተው፥ “ከዚህ ውጣና ሂድ፤ ሄሮ​ድስ ሊገ​ድ​ልህ ይሻ​ልና” አሉት።


ጢባ​ር​ዮስ ቄሣር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አም​ስት ዓመት ጴን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ የይ​ሁዳ ገዢ ሆኖ ሳለ፥ ሄሮ​ድ​ስም በገ​ሊላ የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ሳለ፥ ወን​ድሙ ፊል​ጶ​ስም የኢ​ጡ​ር​ያ​ስና የጥ​ራ​ኮ​ኒ​ዶስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ፥ ሊሳ​ን​ዮ​ስም የሳ​ብ​ላ​ኒስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ ሆነው ሳሉ፥


ይህም የእ​ርሱ ዜና በይ​ሁዳ ሀገ​ሮች ሁሉና በአ​ው​ራ​ጃዋ ሁሉ ተሰማ።


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ነው የሚ​ሉህ አሉ፤ ኤል​ያስ ነው የሚ​ሉ​ህም አሉ፤ ከቀ​ደ​ሙት ነቢ​ያት አንዱ ተነ​ሥ​ቶ​አል የሚ​ሉ​ህም አሉ” አሉት።


ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና፤ ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ራሱ ፈቃድ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ጸጋ በመ​ስ​ጠት፥ በም​ል​ክ​ትና በድ​ንቅ ነገር፥ በልዩ ልዩ ተአ​ም​ራ​ትም መሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው፤ ነገ​ራ​ቸ​ው​ንም አስ​ረ​ዳ​ላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች