Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 15:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤” አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 አይተን እናምን ዘንድ ይህ ክርስቶስ፣ ይህ የእስራኤል ንጉሥ እስኪ ከመስቀል ይውረድ።” ከርሱ ጋራ የተሰቀሉትም እንደዚሁ የስድብ ናዳ ያወርዱበት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 አይተን እናምን ዘንድ ይህ ክርስቶስ፥ ይህ የእስራኤል ንጉሥ እስቲ ከመስቀል ይውረድ።” ከእርሱ ጋር የተሰቀሉትም እንደዚሁ የስድብ ናዳ ያወርዱበት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 እርሱ መሲሑ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ እስቲ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እንይና እንመንበት!” እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎች ይሰድቡት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 15:32
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የሚ​ቤ​ዥም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አም​ላክ የለም።


እግዚአብሔር ፍርድሽን አስወግዶአል፥ ጠላትሽንም ጥሎአል፣ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉ ነገርን አታዪም።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው።


“ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እናምንበታለን።


ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎች ደግሞ ያንኑ እያሉ ይነቅፉት ነበር።


የክሱ ጽሕፈትም “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ተጽፎ ነበር።


ከእርሱም ጋር ሁለት ወንበዴዎች አንዱን በቀኙ አንዱንም በግራው ሰቀሉ።


ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በየት ታው​ቀ​ኛ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ገና ፊል​ጶስ ሳይ​ጠ​ራህ በበ​ለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይ​ች​ሃ​ለሁ” አለው።


የዘ​ን​ባባ ዛፍ ዝን​ጣፊ ይዘው “ሆሣ​ዕና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ቡሩክ ነው” እያሉ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉት።


የማ​ያ​ምኑ ቢኖ​ሩስ የእ​ነ​ርሱ አለ​ማ​መን ሌላ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ምን ይከ​ለ​ክ​ላ​ልን? አይ​ከ​ለ​ክ​ልም።


እነዚህም “ትንሣኤ ከአሁን በፊት ሆኖአል፤” እያሉ ስለ እውነት ስተው የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች