Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 14:72 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

72 ጴጥሮስንም ኢየሱስ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ያለው ቃል ትዝ አለው፤ ነገሩንም አስቦ አለቀሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

72 ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ። ጴጥሮስም፣ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው። ከዚያም ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

72 ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ። ጴጥሮስም፥ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው። ከዚያም ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

72 ወዲያውኑ ዶሮ ሁለተኛ ጊዜ ጮኸ፤ ጴጥሮስም “ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ፥ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ሲል ኢየሱስ የተናገረው ቃል ትዝ አለውና ምርር ብሎ አለቀሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

72 ጴጥሮስንም ኢየሱስ፦ ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው ቃል ትዝ አለው፤ ነገሩንም አስቦ አለቀሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 14:72
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝ​ቡ​ንም ከቈ​ጠረ በኋላ ዳዊ​ትን ልቡ መታው፤ ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ባደ​ረ​ግ​ሁት ነገር እጅግ በድ​ያ​ለሁ፤ አሁን ግን አቤቱ! ታላቅ ስን​ፍና አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​አት ታርቅ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


ታስቢ ዘንድ፥ ታፍ​ሪም ዘንድ፥ ደግ​ሞም ስላ​ደ​ረ​ግ​ሽው ነገር ሁሉ ይቅር ባል​ሁሽ ጊዜ፥ስለ ኀፍ​ረ​ትሽ አፍ​ሽን ትከ​ፍቺ ዘንድ አይ​ቻ​ል​ሽም፤” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ክፉ​ውን መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና መል​ካም ያይ​ደ​ለ​ውን ሥራ​ች​ሁ​ንም ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁና ስለ ርኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ራሳ​ች​ሁን ትጸ​የ​ፋ​ላ​ችሁ።


ከእ​ነ​ር​ሱም የሚ​ሸሹ ይድ​ናሉ፤ መብ​ረ​ርን እን​ደ​ሚ​ማር ርግ​ብም በተ​ራራ ላይ ይሆ​ናሉ፤ እኔም በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ።


ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፤ በዚች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው።


ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው።


እርሱ ግን “የምትዪውን አላውቅም፤ አላስተውልምም፤” ብሎ ካደ። ወደ ውጭም ወደ ደጅ ወጣ፤ ዶሮም ጮኸ።


እርሱ ግን “ይህን የምትሉትን ሰው አላውቀውም፤” ብሎ እራሱን ይረግምና ይምል ጀመር። ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ።


ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! የም​ት​ለ​ውን አላ​ው​ቅም” አለው፤ እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ያን​ጊዜ ዶሮ ጮኸ።


ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ውጭ ወጥቶ መራራ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ።


ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተብሎ የሚ​ደ​ረግ ኀዘን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የሚ​ያ​ሰጥ ንስሓ ነው። ስለ ዓለም የሚ​ደ​ረግ ኀዘን ግን ሞትን ያመ​ጣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች