Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 13:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኀይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “በዚያ ጊዜም የሰው ልጅ በታላቅ ኀይልና ግርማ በደመና ሲመጣ ያዩታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በታላቅ ኋይልና ግርማ በደመና ሲመጣ ያዩታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ከዚያም በኋላ የሰው ልጅ በታላቅ ኀይልና ክብር በደመና ሲመጣ ይታያል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 13:26
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።


እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።”


የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤


“የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤


ኢየሱስም “እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ፤” አለ።


በዚህም በዘማዊና በኀጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።


እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔር መንግሥት በኀይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ፤” አላቸው።


ያን​ጊ​ዜም በሰ​ማይ ደመና፥ በፍ​ጹም ኀይ​ልና ክብር ሲመጣ የሰ​ውን ልጅ ያዩ​ታል።


እነ​ር​ሱም፥ “እና​ንተ የገ​ሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየ​አ​ያ​ችሁ ለምን ቆማ​ች​ኋል? ይህ ከእ​ና​ንተ ወደ ሰማይ ያረ​ገው ኢየ​ሱስ፥ ከእ​ና​ንተ ወደ ሰማይ ሲያ​ርግ እን​ዳ​ያ​ች​ሁት እን​ዲሁ ዳግ​መኛ ይመ​ጣል” አሏ​ቸው።


ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፤ ክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤


የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና መምጣት አስታወቅናችሁ።


እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዐይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፤ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፤ አሜን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች