Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 13:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዐይነት ይሆናልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በእነዚያ ቀናት፣ እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ እስከ አሁን ድረስ፣ ከዚህም በኋላ ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ፍጥረትን ከፈጠረበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ፥ እንዲሁ ደግሞም ወደ ፊት አቻ የሌለው ታላቅ መከራ ይሆናልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በዚያን ወራት እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ መከራ ይሆናል፤ ወደ ፊትም እሱን የሚመስል ጭንቀት ከቶ አይደርስም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 13:19
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ላሜድ። እና​ንተ መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ! በእ​ና​ንተ ዘንድ ምንም የለ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቀ​በት በእኔ ላይ እንደ ተደ​ረ​ገው እንደ እኔ ቍስል የሚ​መ​ስል ቍስል እን​ዳለ ተመ​ል​ከቱ፤ እዩም።


ሜም። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሻ​ለሁ? በም​ንስ እመ​ስ​ል​ሻ​ለሁ? ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድ​ን​ሻል? ማንስ ያጽ​ና​ና​ሻል? ስብ​ራ​ትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚ​ፈ​ው​ስሽ ማን ነው?


ዋው። የማ​ንም እጅ ሳይ​ወ​ድ​ቅ​ባት ድን​ገት ከተ​ገ​ለ​በ​ጠች፥ ከሰ​ዶም ኀጢ​አት ይልቅ የወ​ገኔ ሴት ልጅ ኀጢ​አት በዛች።


የጨ​ለ​ማና የነ​ፋስ ቀን፥ የደ​መ​ናና የጉም ቀን ነው፤ ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ወገ​ግታ ተዘ​ር​ግ​ቶ​አል፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይ​ሆ​ንም።


በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።


ከፍጥረት መጀመሪያ ግን እግዚአብሔር ወንድና ሴት አደረጋቸው፤


ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤


ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን፥ የዘ​ር​ህ​ንም መቅ​ሠ​ፍት፥ ታላ​ቅና የሚ​ያ​ስ​ፈራ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ ለብዙ ጊዜ የሚ​ኖር ክፉ ደዌና ሕማ​ምን ሁሉ ያመ​ጣ​ብ​ሃል።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰውን በም​ድር ላይ ከፈ​ጠ​ረው ጀምሮ፥ ከሰ​ማይ ዳር እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ከቶ እን​ዲህ ያለ ታላቅ ነገር ሆኖ፥ ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰ​ምቶ እንደ ሆነ ከአ​ንተ በፊት የነ​በ​ረ​ውን የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን ጠይቅ።


እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። አለኝም “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች