Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 10:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረኝ” እያለ አብዝቶ ጮኸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፣ “የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ የባሰ ጮኸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፥ “የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ የባሰ ጮኸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 ብዙዎቹ “ዝም በል!” ብለው ገሠጹት፤ እርሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” እያለ ይበልጥ ጮኸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፦ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 10:48
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ንተ ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ በፍ​ጹም ልባ​ች​ሁም ከሻ​ች​ሁኝ ታገ​ኙ​ኛ​ላ​ችሁ።


በዚያን ጊዜ እጁን እንዲጭንባቸውና እንዲጸልይ ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ገሠጹአቸው።


ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ፥ ማረን” እያሉ አብዝተው ጮኹ።


ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረን፤” ብለው እየጮሁ ተከተሉት።


እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ያመጡአቸውን ገሠጹአቸው።


እርሱም ገና ሲናገር ከምኵራብ አለቃው ቤት ዘንድ የመጡት “ልጅህ ሞታለች፤ ስለ ምን መምህሩን አሁን ታደክመዋለህ?” አሉት።


የሚ​መ​ሩ​ትም ዝም እን​ዲል ገሠ​ጹት፤ እርሱ ግን በጣም ጮኾ፥ “የዳ​ዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ” አለ።


በጸ​ሎ​ትና በም​ልጃ ሁሉ ዘወ​ትር በመ​ን​ፈስ ጸልዩ፤ ከዚ​ህም ጋር ስለ ቅዱ​ሳን ሁሉ ለመ​ጸ​ለይ ሁል​ጊዜ ትጉ፤


እር​ሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ፥ በታ​ላቅ ጩኸ​ትና እንባ ከሞት ሊያ​ድ​ነው ወደ​ሚ​ች​ለው ጸሎ​ት​ንና ምል​ጃን አቀ​ረበ፤ ጽድ​ቁ​ንም ሰማው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች