Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 21:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነሡ ሊመ​ል​ሱ​ላ​ች​ሁና ሊከ​ራ​ከ​ሯ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ችሉ እኔ አፍ​ንና ጥበ​ብን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ተቃዋሚዎቻችሁ ሁሉ ሊቋቋሙትና ሊያስተባብሉት የማይችሉትን ቃልና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ተቃዋሚዎቻችሁ በሙሉ ሊቃወሙትና ሊከራከሩት የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከጠላቶቻችሁ ማንም ሊቋቋመው ወይም ሊቃወመው የማይችለውን አንደበትና ጥበብ እኔ እሰጣችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 21:15
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከፊቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጁን ዘር​ግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “እነሆ፥ ቃሌን በአ​ፍህ ውስጥ አኑ​ሬ​አ​ለሁ፤


“በዚያ ቀን ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ቀን​ድን አበ​ቅ​ላ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለአ​ንተ የተ​ከ​ፈተ አፍን እሰ​ጥ​ሀ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


ያን​ጊዜ በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ና​ገ​ረው መን​ፈስ ቅዱስ ነውና።”


ወላ​ጆ​ቻ​ች​ሁና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ፥ ወዳ​ጆ​ቻ​ች​ሁና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል።


ከዚ​ህም በኋላ መጻ​ሕ​ፍ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ተ​ውሉ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ከፈ​ተ​ላ​ቸው።


ሁሉም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተሞሉ፤ ይና​ገሩ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እንደ አደ​ላ​ቸው መጠ​ንም እየ​ራ​ሳ​ቸው በሀ​ገሩ ሁሉ ቋንቋ ይና​ገሩ ጀመሩ።


እር​ሱም ስለ ጽድ​ቅና ስለ ንጽ​ሕና፥ ስለ​ሚ​መ​ጣ​ውም ኵነኔ በነ​ገ​ራ​ቸው ጊዜ በዚህ የተ​ነሣ ፊል​ክስ ፈራና ጳው​ሎ​ስን፥ “አሁ​ንስ ሂድ፤ በተ​መ​ቸ​ኝም ጊዜ ልኬ አስ​ጠ​ራ​ሃ​ለሁ” አለው።


አግ​ሪ​ጳም ጳው​ሎ​ስን፥ “አሁ​ንስ ወደ ክር​ስ​ቲ​ያ​ን​ነት ልታ​ገ​ባኝ ጥቂት ብቻ ቀር​ቶ​ሃል” አለው።


ነገር ግን ይቃ​ወ​ሙት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ በጥ​በ​ብና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበ​ርና።


ለእ​ኔም፦ ቃልን እን​ዲ​ሰ​ጠኝ፥ አፌ​ንም ከፍቼ የወ​ን​ጌ​ልን ምሥ​ጢር በግ​ልጥ እን​ድ​ና​ገር ጸል​ዩ​ልኝ።


ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች