Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 20:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ብለው ጠየ​ቁት፥ “መም​ህር ሆይ፥ ሙሴ፦ ‘ወን​ድሙ ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሚስ​ቱን ትቶ የሞ​ተ​በት ሰው ቢኖር ወን​ድሙ ሚስ​ቱን አግ​ብቶ ለወ​ን​ድሙ ዘር ይተካ’ ሲል ጽፎ​ል​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እንዲህም አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፣ ወንድሙ የሟችን ሚስት አግብቶ ልጆች በመውለድ ለወንድሙ ዘር እንዲተካ ሙሴ ጽፎልናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እንዲህም አሉ፤ “መምህር ሆይ! ሙሴ ‘አንድ ሰው ባለትዳር ወንድም ቢኖረውና፥ እርሱም ሳይወልድ ቢሞት፥ ወንድሙ የእርሱን ሚስት አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፤’ ብሎ ጻፈልን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 “መምህር ሆይ! ሙሴ እንዲህ ሲል ጽፎልናል፤ ‘አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሚስቱ በሞት ቢለይ ወንድሙ ሴትዮዋን አግብቶ ለሟቹ ዘር ያትርፍለት።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እንዲህ ሲሉ፦ መምህር ሆይ፥ ሙሴ፦ ሚስት ያለችው የአንድ ሰው ወንድም ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ ብሎ ጻፈልን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 20:28
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይሁ​ዳም ምራ​ቱን ትዕ​ማ​ርን፥ “ልጄ ሴሎም እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በአ​ባ​ትሽ ቤት መበ​ለት ሆነሽ ተቀ​መጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወን​ድ​ሞቹ እን​ዳ​ይ​ሞ​ት​ብኝ ብሎ​አ​ልና። ትዕ​ማ​ርም ሄዳ በአ​ባቷ ቤት ተቀ​መ​ጠች።


ይሁ​ዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕ​ማር እው​ነ​ተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎ​ምን አል​ሰ​ጠ​ኋ​ት​ምና” አለ። ትገ​ደል ማለ​ት​ንም ተወ፤ ደግ​ሞም አላ​ወ​ቃ​ትም።


ይሁ​ዳም አው​ና​ንን፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ሚስት ግባ፤ አግ​ባ​ትም፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ዘርን አቁ​ም​ለት” አለው።


እን​ግ​ዲህ ከእኛ ዘንድ ሰባት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነበሩ፤ ታላቁ ሚስት አግ​ብቶ ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሞተ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች