Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 7:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ፍር​ም​ባ​ው​ንና የቀኝ ወር​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ ለካ​ህኑ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆ​ቹም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት ላይ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች ወስጃለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ከእስራኤላውያን የሚያገኙት መደበኛ ድርሻቸው እንዲሆን ሰጥቻቸዋለሁ።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 የሚወዘወዘውን ፍርምባና እንደ ቁርባን የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከሰላም መሥዋዕታቸው ወስጄ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ድርሻ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ እነርሱን ሰጥቼአቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ከእስራኤላውያን የአንድነት መሥዋዕት መካከል የተወዘወዘውን ፍርንባና የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤላውያን እንደሚቀርብላቸው ቋሚ ድርሻ አድርጌ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 የሚወዘወዘውን ፍርምባና የሚነሣውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕታቸው ወስጄአለሁ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘላለም እድል ፈንታ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ሰጥቼአቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 7:34
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ለአ​ሮ​ንም ክህ​ነት የታ​ረ​ደ​ውን የአ​ው​ራ​ውን በግ ፍር​ምባ ወስ​ደህ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም የአ​ንተ ወግ ይሆ​ናል።


በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም ታስ​ታ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቆብ​ንም ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐ​ትም ክህ​ነት ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም የአ​ሮ​ን​ንና የል​ጆ​ቹን እጆች ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።


ስብና ደም እን​ዳ​ት​በሉ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።”


ከአ​ሮ​ንም ልጆች የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ደሙ​ንና ስቡን ለሚ​ያ​ቀ​ርብ ለእ​ርሱ ቀኝ ወርቹ እድል ፈን​ታው ይሆ​ናል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​አ​ቸው የተ​ቀ​ደሱ ነገ​ሮች ሁሉ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ለካ​ህኑ ነው።


ካህ​ኑም እነ​ዚ​ህን ሁሉ ቍር​ባን አድ​ርጎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​ባል፤ ይህም የቍ​ር​ባን ፍር​ም​ባና የመ​ባው ወርች ለካ​ህኑ የተ​ቀ​ደሰ ነው፤ ከዚ​ያም በኋላ ባለ​ስ​እ​ለቱ ወይን ይጠ​ጣል።


አሮ​ንም ሌዋ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ስጦታ አድ​ርጎ፥ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይለ​ያ​ቸ​ዋል።


በሬ ወይም በግ ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሕዝብ የካ​ህ​ናቱ ወግ ይህ ይሆ​ናል፤ ወር​ቹ​ንና ሁለ​ቱን ጕን​ጮ​ቹን፥ ጨጓ​ራ​ው​ንም ለካ​ህኑ ይሰ​ጣሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች