Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባለው በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ላይ ከደሙ ያደ​ር​ጋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ባለው ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከደሙ ጥቂት ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በእግዚአብሔር ፊት ያለውን የመሠዊያ ቀንዶች ይቅባ፤ የተረፈውን ደም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ባለው በሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ግርጌ ያፍስሰው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በመገናኛውም ድንኳን ውስጥ በጌታ ፊት ባለው በመሠዊያው ቀንዶች ላይ ከደሙ ያደርጋል፤ ደሙንም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጅ ባለው የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ በታች ያፈስሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ደግሞም ጥቂት ደም ወስዶ በድንኳኑ በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ባለው በመሠዊያው ጒጦች ላይ ያኑር፤ ከዚያም የተረፈውን ደም በድንኳኑ መግቢያ በኩል የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፍስሰው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በመገናኛውም ድንኳን ውስጥ በእግዚአብሔር ፊት ባለው በዕጣን መሠዊያው ቀንዶች ላይ ከደሙ ያደርጋል፤ ደሙንም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጅ ባለው ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ በታች ያፈስሰዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 4:18
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወይ​ፈ​ኖ​ቹ​ንም አረዱ፤ ካህ​ና​ቱም ደሙን ተቀ​ብ​ለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጩት፤ አውራ በጎ​ቹ​ንም አረዱ፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጩት፤ ጠቦ​ቶ​ቹ​ንም አረዱ፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጩት።


ከወ​ይ​ፈ​ኑም ደም ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ላይ በጣ​ትህ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ደም ሁሉ ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ታፈ​ስ​ሰ​ዋ​ለህ።


አሮ​ንም በዓ​መት አንድ ጊዜ በቀ​ን​ዶቹ ላይ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ር​ጋል፤ በዓ​መት አንድ ጊዜ ኀጢ​አ​ትን ከሚ​ያ​ነ​ጻው ደም ይወ​ስ​ዳል፤ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ነጻ ያደ​ር​ጋል፤ ይህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።”


ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


ካህ​ኑም ከደ​ምዋ በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


ካህ​ኑም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለው ጣፋጭ ዕጣን በሚ​ታ​ጠ​ን​በት መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ከደሙ ያደ​ር​ጋል፤ የወ​ይ​ፈ​ኑ​ንም ደም ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ባለው ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


ከኀ​ጢ​አ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ደም በመ​ሠ​ዊ​ያው ግድ​ግዳ ላይ ይረ​ጨ​ዋል፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ደም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች ያን​ጠ​ፈ​ጥ​ፋል፤ እርሱ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።


ነገር ግን በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ይሆን ዘንድ ከደሙ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ገ​ባው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ አይ​በ​ላም፤ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል።


አረ​ዱ​ትም፤ ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀን​ዶች ዙሪያ ቀባ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም አነ​ጻው፤ ደሙ​ንም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች አፈ​ሰ​ሰው፤ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ትም ዘንድ ቀደ​ሰው።


የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ጣቱ​ንም በደሙ ውስጥ ነክሮ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀን​ዶች ቀባ፤ ደሙ​ንም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች አፈ​ሰ​ሰው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች