Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 22:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከአ​ሮን ዘር ለምጽ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሁሉ ንጹሕ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ። ከበ​ድ​ንም የተ​ነሣ ርኩስ የሆ​ነ​ውን፥ ወይም ዘሩ ከእ​ርሱ የሚ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትን የሚ​ነካ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “ ‘ከአሮን ዘር ተላላፊ የቈዳ በሽታ ያለበት ወይም ከሰውነቱ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ማንኛውም ሰው እስኪነጻ ድረስ ቅዱሱን መሥዋዕት አይብላ፤ እንዲሁም በአስከሬን የረከሰውን ነገር ወይም የዘር ፈሳሽ ያለበትን ሰው ቢነካ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከአሮን ዘር ማናቸውም ሰው የለምጽ ደዌ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት፥ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ከተቀደሱት ነገሮች አይብላ። በበድን፥ ወይም ዘሩ በሚፈስስበት ሰው የረከሰውን ነገር የሚነካ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “ከአሮን ተወላጆች ማንም ሰው የሥጋ ደዌ በሽታ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት ከሆነ እስከሚነጻበት ድረስ ከተቀደሰው ነገር አይብላ። በድን በመንካቱ የረከሰውን ነገር የሚነካ ወይም የዘር ፈሳሽ ያለበት

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከአሮን ዘር ለምጽ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት ሁሉ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ከተቀደሰው አይብላ። ከበድንም የተነሣ ርኩስ የሆነውን፥ ወይም ዘሩ ከእርሱ የሚፈስስበትን የሚነካ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 22:4
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ለመ​ብል ከሚ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ እን​ስ​ሳት የሞተ ቢኖር፥ በድ​ኑን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ዘር የነ​ካው ልብስ ሁሉ፥ ቍር​በ​ትም ሁሉ በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።


ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም የተ​ረ​ፈው ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሆ​ናል፤ ይህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የተ​ረፈ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም የተ​ረ​ፈው ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሆ​ናል፤ ይህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የተ​ረፈ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፥ “ከወ​ገ​ና​ቸው በሞተ ሰው ራሳ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ለካ​ህ​ናቱ ለአ​ሮን ልጆች ንገ​ራ​ቸው።


የቅ​ዱ​ሱ​ንና የቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳ​ኑን የአ​ም​ላ​ኩን መባ ይብላ፤


ሐጌም፦ በሬሳ የረከሰ ሰው ከእነዚህ አንዱን ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይረክሳልን? አለ። ካህናቱም፦ አዎን ይረክሳል ብለው መለሱ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ዩ​ትን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን መባ ሁሉ ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም ጋር ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ችህ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ይህም ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግና የሁ​ል​ጊዜ ቃል ኪዳን ነው።”


በእ​ሳት ከሚ​ቀ​ር​በው ከተ​ቀ​ደ​ሰው ይህ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ለእኔ የሚ​ያ​መ​ጡት መባ​ቸው ሁሉ፥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ሁሉ፥ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ፥ የበ​ደ​ላ​ቸ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ፥ ከተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ሁሉ ለአ​ንተ ለል​ጆ​ች​ህም ይሆ​ናል።


“ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለ​መ​ና​ው​ንም ባያ​ነጻ፥ ያ ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ አር​ክ​ሶ​አ​ልና ከማ​ኅ​በሩ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ በሚ​ያ​ነጻ ውኃ አል​ተ​ረ​ጨ​ምና ርኩስ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች