Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ካህ​ኑም ከተ​ፈ​ተ​ገው እህል፥ ከዘ​ይ​ቱም ወስዶ ከዕ​ጣኑ ጋር መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውን ያቀ​ር​ባል፤ ይህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ካህኑም ከተፈተገው እህልና ከዘይቱ ወስዶ፣ ከዕጣኑ ሁሉ ጋራ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መታሰቢያ አድርጎ ያቃጥል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ካህኑም ከተፈተገው እህል ከዘይቱም ወስዶ፥ ከዕጣኑ ሁሉ ጋር መታሰቢያውን ያቃጥላል፤ ይህ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ካህኑም ከዚያ መባ ከፊሉን ወስዶ ለእግዚአብሔር የቀረበ መሆኑን ለማስታወስ ዘይቱንም፥ ዕጣኑንም በሙሉ ከእህሉ ጋር አብሮ ያቃጥለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ካህኑም ከተፈተገው እህል ከዘይቱም ወስዶ ከዕጣኑ ሁሉ ጋር መታሰቢያውን ያቃጥላል፤ ይህ ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 2:16
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልመ​ና​ዬን በፊቱ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ መከ​ራ​ዬ​ንም በፊቱ እና​ገ​ራ​ለሁ።


የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እሰ​ብክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ኛ​ልና፤ ልባ​ቸው የተ​ሰ​በ​ረ​ውን እጠ​ግን ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን፥ ለታ​ሰ​ሩ​ትም መፈ​ታ​ትን፥ ለዕ​ው​ራ​ንም ማየ​ትን እና​ገር ዘንድ ልኮ​ኛል።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ባሉ፤ ካህ​ኑም ሁሉን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።


እነ​ዚ​ህ​ንም ዐሥ​ራት አድ​ር​ጋ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለበጎ መዓዛ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አይ​ቀ​ር​ቡም።


“ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው እህ​ልህ መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብታ​ቀ​ርብ በእ​ሳት የተ​ጠ​በ​ሰና የተ​ፈ​ተገ የእ​ህል እሸት ታቀ​ር​ባ​ለህ።


ዘይ​ትም ታፈ​ስ​ስ​በ​ታ​ለህ፤ ዕጣ​ንም ትጨ​ም​ር​በ​ታ​ለህ፤ የእ​ህል ቍር​ባን ነው።


ካህ​ኑም ከቍ​ር​ባኑ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውን ይወ​ስ​ዳል፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባን ነው።


እር​ሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ፥ በታ​ላቅ ጩኸ​ትና እንባ ከሞት ሊያ​ድ​ነው ወደ​ሚ​ች​ለው ጸሎ​ት​ንና ምል​ጃን አቀ​ረበ፤ ጽድ​ቁ​ንም ሰማው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች