ዘሌዋውያን 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በምስክሩ ታቦት ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመና ውስጥ እገለጣለሁና ወንድምህ አሮን በመጋረጃው ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማለት በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ፊት፣ በፈለገ ጊዜ ሁሉ እንዳይገባና እንዳይሞት ንገረው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና፥ እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደተቀደሰው ስፍራ፥ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 “እኔ በታቦቱ ስርየት መክደኛ በደመና የምገለጥበት ስለ ሆነ፥ መጋረጃውን አልፎ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ያለበት ሁልጊዜ ሳይሆን፥ በአንድ በተወሰነ ቀን ብቻ መሆኑን፥ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው፤ ይህን ትእዛዝ የማይፈጽም ከሆነ ይሞታል፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። ምዕራፉን ተመልከት |