Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 13:57 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

57 በል​ብ​ሱም ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተ​ደ​ረገ ነገር ላይ ደግሞ ቢታይ፥ የወጣ ለምጽ ነው፤ ደዌው ያለ​በ​ትን ነገር ያቃ​ጥ​ሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

57 ነገር ግን ደዌው በልብሱ ወይም በሸማኔ ዕቃ በተሠራው ወይም በእጅ በተጠለፈው ጨርቅ ላይ ወይም ከቈዳ በተሠራው ዕቃ ላይ ቢታይ፣ መስፋፋቱ ስለ ሆነ ደዌው ያለበት ማንኛውም ነገር በእሳት ይቃጠል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

57 በልብሱም ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከተለፋው ቆዳ በተሠራ በማናቸውም ነገር ላይ ዳግም ቢታይ፥ እየሰፋ የሚሄድ ደዌ ነው፤ ደዌው ያለበትን ነገር በእሳት ታቃጥለዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

57 ሻጋታው እንደገና ቢታይ እርሱ እየተስፋፋ የሚሄድ ስለ ሆነ፥ ባለ ንብረቱ ያቃጥለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

57 በልብሱም ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛው በተደረገ ነገር ላይ ደግሞ ቢታይ፥ የወጣ ለምጽ ነው፤ ደዌው ያለበትን ነገር አቃጥለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 13:57
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጽ​ዮን ያሉ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ፈሩ፤ መን​ቀ​ጥ​ቀጥ ዝን​ጉ​ዎ​ችን ያዘ፤ እሳት እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሀገ​ር​ንስ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው?


በድሩ ወይም በማጉ ላይ ቢሆን፥ የበግ ጠጕር ወይም የተ​ልባ እግር ቢሆን፥ ቆዳ ወይም ከቆዳ የሚ​ደ​ረግ ነገር ቢሆን፥


“ካህ​ኑም ቢያይ፥ እነሆ፥ ደዌው ከታ​ጠበ በኋላ ቢከ​ስም፥ ከል​ብሱ ወይም ከድሩ ወይም ከማጉ ወይም ከቆ​ዳው ይቅ​ደ​ደው።


ልብሱ ወይም ድሩ ወይም ማጉ ወይም ከቆዳ የተ​ደ​ረ​ገው ነገር ከታ​ጠበ በኋላ ደዌው ቢለ​ቅ​ቀው ሁለ​ተኛ ጊዜ ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።


ንጉሡም ተቈጣ፤ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።


በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል ‘እናንተ ርጉማን! ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።


መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


“ስለ ለምጽ ደዌ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያስ​ተ​ማ​ሩ​ህን ሁሉ ፈጽ​መህ እን​ድ​ት​ጠ​ብቅ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ግም ተጠ​ን​ቀቅ፤ እኔ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እን​ዲሁ ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።


ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።


ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች