Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 13:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 ልብ​ሱን ያቃ​ጥ​ላል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጕር ወይም የተ​ልባ እግር ቢሆን ወይም ከቆዳ የተ​ደ​ረገ ቢሆን፥ ደዌ ያለ​በት ሁሉ እየ​ፋገ የሚ​ሄድ ለምጽ ነውና በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 ልብሱን ወይም በሸማኔ ዕቃ የተሠራውን ወይም በእጅ የተጠለፈውን የበግ ጠጕር ወይም በፍታ ወይም ደዌው ያለበትን ማንኛውንም ከቈዳ የተሠራ ዕቃ ያቃጥል፤ ደዌው ክፉ ነውና፤ ዕቃው ይቃጠል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 ልብሱን ያቃጥል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጉር ወይም በፍታ ወይም ከተለፋው ቆዳ የሆነ ማናቸውም ደዌው ያለበት ነገር ላይ ቢሆን፥ እየሰፋ የሚሄድ የለምጽ ደዌ ነውና በእሳት ይቃጠል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 ይህም አጥፊ ሻጋታ እየሰፋ የሚሄድ ስለ ሆነ በእሳት ይቃጠል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 ልብሱን ያቃጥል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጕር ወይም በፍታ ቢሆን ወይም ከአጐዛው የተደረገ ቢሆን፥ ደዌ ያለበት ሁሉ፥ እየገፋ የሚሄድ ለምጽ ነውና በእሳት ይቃጠል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 13:52
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በብ​ርም ወደ ተለ​በጡ፥ በወ​ር​ቅም ወደ አጌጡ ወደ ጣዖ​ታቱ እን​ሂድ የሚሉ ናቸው፤ ያን​ጊዜ እንደ ትቢያ የደ​ቀቁ ይሆ​ናሉ፤ እንደ ውኃም ይደ​ፈ​ር​ሳሉ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ጥራ​ጊ​ዎ​ችን ይጥ​ሉ​ባ​ቸ​ዋል።


ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳች በው​ስጡ የወ​ደ​ቀ​በ​ትን የሸ​ክ​ላ​ውን ዕቃ ሁሉ ስበ​ሩት፤ በው​ስ​ጡም ያለው ሁሉ ርኩስ ነው።


ከእ​ነ​ዚ​ህም በድን የሚ​ወ​ድ​ቅ​በት ሁሉ ርኩስ ነው፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰ​ባ​በ​ራል፤ ርኩ​ሳን ናቸ​ውና፤ ለእ​ና​ንተ ርኩ​ሳን ይሆ​ናሉ።


“የለ​ም​ጽም ደዌ በል​ብስ ላይ ቢሆን፥ ልብ​ሱም የበግ ጠጕር ወይም የተ​ልባ እግር ቢሆን፥


በድሩ ወይም በማጉ ላይ ቢሆን፥ የበግ ጠጕር ወይም የተ​ልባ እግር ቢሆን፥ ቆዳ ወይም ከቆዳ የሚ​ደ​ረግ ነገር ቢሆን፥


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደዌ​ውን ያያል፤ ደዌ​ውም በል​ብስ ላይ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም በቆ​ዳው ወይም ከቆ​ዳው በሚ​ደ​ረግ ነገር ቢሰፋ፥ ደዌው እየ​ፋገ የሚ​ሄድ ለምጽ ነው፤ ርኩስ ነው።


“ካህኑ ቢያይ፥ እነ​ሆም፥ ደዌው በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተ​ደ​ረገ ነገር ቢሆን በል​ብሱ ላይ ባይ​ሰፋ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች