Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሰቈቃወ 2:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ጻዴ። ልባ​ቸው ወደ ጌታ ጮኸ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እን​ባ​ሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍ​ስሺ፤ ለሰ​ው​ነ​ትሽ ዕረ​ፍት አት​ስጪ፤ የዐ​ይ​ን​ሽ​ንም ብሌን አታ​ቋ​ርጪ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የሕዝቡ ልብ፣ ወደ ጌታ ጮኸ። የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፤ ቀንና ሌሊት፣ እንባሽ እንደ ወንዝ ይፍሰስ፤ ለራስሽ ዕረፍትን አትስጪ፣ ዐይኖችሽ ከማንባት አያቋርጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጻዴ። ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፥ ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፥ የዐይንሽ ብሌን አታቋርጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በኢየሩሳሌም ቅጥር ውስጥ የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር ጩኹ! ዕንባችሁም ሌሊትና ቀን እንደ ጐርፍ ይውረድ፤ በፍጹም ዕረፍት አታድርጉ፤ ለዐይኖቻችሁም ፋታን አትስጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ጻዴ። ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፥ ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፥ የዓይንሽ ብሌን አታቋርጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሰቈቃወ 2:18
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህን ባት​ሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕ​ቢ​ታ​ችሁ በስ​ውር ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መንጋ ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ዐይኔ ታነ​ባ​ለች፤ እን​ባ​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ለች።


“እን​ደ​ዚ​ህም ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የወ​ገኔ ልጅ ድን​ግ​ሊቱ በታ​ላቅ ስብ​ራ​ትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ ሌሊ​ትና ቀን ሳያ​ቋ​ርጡ እን​ባን ያፍ​ስሱ።


እን​ደ​ም​ታ​ምጥ፥ የበ​ኵር ልጅ​ዋ​ንም እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸ​ት​ሽን ሰም​ቻ​ለ​ሁና፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድ​ካም ሰለለ፤ እጆ​ች​ዋ​ንም ትዘ​ረ​ጋ​ለች፤ ተገ​ድ​ለው ከሞ​ቱት የተ​ነሣ ነፍሴ ዝላ​ለ​ችና ወዮ​ልኝ! አለች።


ስለ ተገ​ደሉ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊ​ትና ቀን አለ​ቅስ ዘንድ ለራሴ ውኃን፥ ለዐ​ይ​ኔም የዕ​ን​ባን ምንጭ ማን በሰ​ጠኝ?


ዔ። የሚ​ያ​ጽ​ና​ናኝ፥ ነፍ​ሴ​ንም የሚ​መ​ል​ሳት ከእኔ ርቆ​አ​ልና ዐይኔ ውኃ ያፈ​ስ​ሳል። ጠላት በር​ት​ቶ​አ​ልና ልጆች ጠፍ​ተ​ዋል።


ቤት። በሌ​ሊት እጅግ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ እን​ባ​ዋም በጉ​ን​ጭዋ ላይ አለ፤ ከሚ​ያ​ፈ​ቅ​ሩ​አት ሁሉ የሚ​ያ​ጽ​ና​ናት የለም፤ ወዳ​ጆ​ች​ዋም ሁሉ ወነ​ጀ​ሉ​አት፤ ጠላ​ቶ​ችም ሆኑ​አት።


ሔት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈ​ርስ ዘንድ ዐሰበ፤ የመ​ለ​ኪ​ያ​ው​ንም ገመድ ዘረጋ፤ እር​ስ​ዋን ከማ​ጥ​ፋት እጁን አል​መ​ለ​ሰም፤ ምሽ​ጉና ቅጥሩ አለ​ቀሱ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ደከሙ።


በመ​ኝ​ታ​ቸው ላይ ሆነው ያለ​ቅሱ ነበር እንጂ በል​ባ​ቸው ወደ እኔ አል​ጮ​ኹም፤ ስለ እህ​ልና ስለ ወይን ይገ​ዳ​ደሉ ነበር፤


ድንጋይም ከግንብ ውስጥ ይጮኻል፥ እንጨትም ከውቅር ውስጥ ይመልስለታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች