Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 8:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው በሙ​ዳየ ምጽ​ዋት አጠ​ገብ ይህን ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ያ​ዙ​ትም፤ ጊዜው ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ኢየሱስ ይህን የተናገረው በቤተ መቅደሱ ግቢ፣ በግምጃ ቤት አጠገብ ሲያስተምር ነበር፤ ይሁን እንጂ ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም አልያዘውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር በግምጃ ቤት አጠገብ ይህንን ነገር ተናገረ፤ ጊዜው ገና አልደረሰምና ማንም አልያዘውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ኢየሱስ ይህን ቃል የተናገረው በቤተ መቅደስ በገንዘብ መቀበያ ሣጥን አጠገብ ሆኖ ሲያስተምር ነው። ታዲያ፥ ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም አልያዘውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተም በግምጃ ቤት አጠገብ ይህን ነገር ተናገረ፤ ጊዜው ገና አልደረሰምና ማንም አልያዘውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 8:20
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ዚህ አራቱ ኀያ​ላን ሰዎች ለአ​ራቱ በሮች ኀላ​ፊ​ዎች ነበሩ። ሌዋ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ባሉ ጓዳ​ዎ​ችና ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ የተ​ሾሙ ነበሩ።


በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።


የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው “የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም፤” አሉ።


ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ በመዝገብ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ ያይ ነበር፤ ብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር፤


ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ “እውነት እላችኋለሁ፤ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች፤


ያን ጊዜም የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎች ሊይ​ዙት ወደዱ፤ ይህን ስለ እነ​ርሱ እንደ መሰለ ዐው​ቀ​ዋ​ልና፤ ነገር ግን ሕዝ​ቡን ፈሩ​አ​ቸው።


በሙ​ዳየ ምጽ​ዋቱ መባ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ገቡ ባለ​ጠ​ጎ​ችን አየ።


ዳግ​መ​ኛም ሊይ​ዙት ፈለጉ፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም አመ​ለጠ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንቺ ሆይ ካንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰም” አላት።


በበ​ዓሉ ቀኖች እኩ​ሌ​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ መቅ​ደስ ወጥቶ ያስ​ተ​ምር ጀመረ።


ስለ​ዚ​ህም ሊይ​ዙት ወደው ነበር፤ ነገር ግን እጁን በእ​ርሱ ላይ ያነሣ የለም፤ ጊዜዉ ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና።


ከእ​ነ​ር​ሱም ሊይ​ዙት የወ​ደዱ ነበሩ፤ ነገር ግን በእ​ርሱ ላይ እጁን ያነሣ የለም።


እና​ን​ተም ወደ​ዚህ በዓል ውጡ፤ እኔ አሁን ወደ​ዚህ በዓል አል​ወ​ጣም፤ ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰ​ምና።”


በጥ​ዋ​ትም ገስ​ግሦ ዳግ​መኛ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እር​ሱም ተቀ​ምጦ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመር።


ሊደ​በ​ድ​ቡ​ትም ድን​ጋይ አነሡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ተሰ​ወ​ራ​ቸው፤ ከቤተ መቅ​ደ​ስም ወጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አልፎ ሄደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች