Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የሁ​ለት ሰዎች ምስ​ክ​ር​ነት የታ​መነ እንደ ሆነ በሕ​ጋ​ችሁ ተጽ​ፎ​አል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የሁለት ሰዎች ምስክርነት ተቀባይነት እንዳለው በሕጋችሁ ተጽፏል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የሁለት ሰዎችም ምስክርነት እውነት እንደሆነ በሕጋችሁ ትጽፎአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የሁለት ሰዎች ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ በሕጋችሁ ተጽፎአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የሁለት ሰዎችም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ በሕጋችሁ ትጽፎአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 8:17
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳግ​መ​ኛም ወልደ አዴር እን​ዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝ​ቤና ሠራ​ዊቴ ሁሉ ሀገ​ር​ህን ሰማ​ር​ያን ባያ​ጠ​ፉት፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ ባያ​ደ​ር​ጉት አማ​ል​ክት እን​ዲህ ያድ​ር​ጉ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ሉኝ።”


ነፍሰ ገዳይ ሁሉ በም​ስ​ክ​ሮች ቃል ይገ​ደ​ላል፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን ማና​ቸ​ው​ንም ሰው መግ​ደል አይ​ገ​ባም።


ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አማ​ል​ክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በኦ​ሪ​ታ​ችሁ ተጽፎ የለ​ምን?


ነገር ግን በኦ​ሪ​ታ​ቸው፦ በከ​ንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።


ወደ እና​ንተ ስመጣ እነሆ ይህ ሦስ​ተ​ኛዬ ነው፤ ነገር ሁሉ፥ በሁ​ለት ወይም በሦ​ስት ምስ​ክር አፍ የሚ​ጸና አይ​ደ​ለ​ምን?


እን​ግ​ዲህ ኦሪት በእ​ርሱ በማ​መን እን​ጸ​ድቅ ዘንድ ወደ ክር​ስ​ቶስ መሪ ሆነ​ችን።


በኦ​ሪት ሕግ እን​ኑር ትላ​ላ​ች​ሁን? ኦሪ​ትን አት​ሰ​ሙ​አ​ት​ምን?


በሁ​ለት ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ሞት የሚ​ገ​ባ​ቸው ይገ​ደሉ፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን አይ​ገ​ደሉ።


“ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማ​ድ​ረ​ግም ስለ​ሚ​ሠ​ራት ኀጢ​አት ሁሉ በማ​ንም ላይ አንድ ምስ​ክር አይ​ሁን፤ በሁ​ለት ምስ​ክ​ሮች ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ቃል ነገር ሁሉ ይጸ​ናል።


ከሙሴ ሕግ የተ​ላ​ለፈ ቢኖር ሁለት፥ ወይም ሦስት ምስ​ክ​ሮች ከመ​ሰ​ከ​ሩ​በት ያለ ምሕ​ረት ይሞ​ታል።


የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።


ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች