Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 7:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ‘ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ አታ​ገ​ኙ​ኝ​ምም፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም’ የሚ​ለን ይህ ነገር ምን​ድን ነው?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ‘ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበትም ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ይሆን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ‘ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤’ የሚለውስ ይህ አባባል ምን ማለት ነው?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ‘ትፈልጉኛላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ነው?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እርሱ፦ “ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም የሚለው ይህ ቃል ምንድር ነው?” ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 7:36
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝ​ቡም፥ “እኛስ ክር​ስ​ቶስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ኖር በኦ​ሪት ሰም​ተን ነበር፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አንተ ‘የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ አለው’ ትለ​ና​ለህ? እን​ግ​ዲህ ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለ​ሱ​ለት።


ልጆች ሆይ፥ ገና ጥቂት ጊዜ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ፤ ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ለአ​ይ​ሁ​ድም እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አይ​ቻ​ላ​ች​ሁም እን​ዳ​ል​ኋ​ቸው፥ አሁ​ንም ለእ​ና​ንተ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም፥ “ሰው ከሸ​መ​ገለ በኋላ ዳግ​መኛ መወ​ለድ እን​ደ​ምን ይች​ላል? ዳግ​መኛ ይወ​ለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅ​ፀን ተመ​ልሶ መግ​ባት ይች​ላ​ልን?” አለው።


ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም መልሶ፥ “ይህ ሊሆን እን​ዴት ይቻ​ላል?” አለው።


አይ​ሁ​ድም ስለ እርሱ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፤ “ከሰ​ማይ የወ​ረደ የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ” ብሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ እን​በላ ዘንድ ሥጋ​ውን ሊሰ​ጠን እን​ዴት ይች​ላል?” ብለው እርስ በር​ሳ​ቸው ተከ​ራ​ከሩ።


ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ብዙ​ዎቹ ይህን ሰም​ተው፥ “ይህ ነገር የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ነው፤ ማንስ ሊሰ​ማው ይች​ላል?” አሉ።


ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ አታ​ገ​ኙ​ኝ​ምም፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በ​ትም እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም።”


ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “እኔ እሄ​ዳ​ለሁ ትሹ​ኛ​ላ​ች​ሁም፤ ነገር ግን አታ​ገ​ኙ​ኝም፤ በኀ​ጢ​ኣ​ታ​ች​ሁም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በ​ትም እና​ንተ መም​ጣት አይ​ቻ​ላ​ች​ሁም” አላ​ቸው።


ለሥ​ጋዊ ሰው ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነገር ሞኝ​ነት ይመ​ስ​ለ​ዋ​ልና፥ አይ​ቀ​በ​ለ​ውም፤ በመ​ን​ፈ​ስም የሚ​መ​ረ​መር ስለ​ሆነ ሊያ​ውቅ አይ​ች​ልም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች