Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 6:53 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

53 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ የሰ​ውን ልጅ ሥጋ ካል​በ​ላ​ችሁ፥ ደሙ​ንም ካል​ጠ​ጣ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የላ​ች​ሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

53 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ የሰውን ልጅ ሥጋውን ካልበላችሁና ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

53 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በእራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

53 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ፥ ደሙንም ካልጠጣችሁ ሕይወት የላችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

53 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 6:53
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲህም አለ “እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።


እውነት እላችኋለሁ፤ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፤ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።


ኢየሱስም “ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፤ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም፤” አለው።


አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።


አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “መቼም ቢሆን አንተ እግ​ሬን አታ​ጥ​በ​ኝም” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ እኔ እግ​ር​ህን ካላ​ጠ​ብ​ሁህ ከእኔ ጋር ዕድል ፋንታ የለ​ህም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእ​ና​ንተ፤ ቅር​ን​ጫፍ በወ​ይኑ ግንድ ከአ​ል​ኖረ ብቻ​ውን ሊያ​ፈራ እን​ደ​ማ​ይ​ችል እና​ን​ተም እን​ዲሁ በእኔ ካል​ኖ​ራ​ችሁ ፍሬ ማፍ​ራት አት​ች​ሉም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ለማ​የት አይ​ች​ልም” አለው።


በወ​ልድ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው፤ በወ​ልድ የማ​ያ​ምን ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቍጣ መቅ​ሠ​ፍት በላዩ ይኖ​ራል እንጂ ሕይ​ወ​ትን አያ​ይም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ከው​ኃና ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ሊገባ አይ​ች​ልም።


እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በእኔ የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት አለው።


“ከሰ​ማይ የወ​ረደ የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እን​ጀራ የሚ​በላ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፤ ስለ ዓለም ሕይ​ወት የም​ሰ​ጠው ይህ እን​ጀራ ሥጋዬ ነው።”


ሥጋዬ እው​ነ​ተኛ መብል ነውና፤ ደሜም እው​ነ​ተኛ መጠጥ ነውና።


እን​ግ​ዲህ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበ​ረ​በት ሲያ​ርግ ብታ​ዩት እን​ዴት ይሆን?


ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች