Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከጠ​ገ​ቡም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን፥ “ከቍ​ር​ስ​ራሹ ምንም የሚ​ወ​ድቅ እን​ዳ​ይ​ኖር የተ​ረ​ፈ​ውን ቍር​ስ​ራሽ አንሡ፤” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሁሉም በልተው ከጠገቡ በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱን፣ “ከተረፈው ቍርስራሽ ምንም እንዳይባክን ሰብስቡ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “አንድም እንኳን እንዳይጠፋ የተረፈውን ቁርስራሽ አከማቹ፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሁሉም በልተው ከጠገቡ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፥ “አንድም ነገር እንዳይባክን የተረፈውንም ፍርፋሪ ሰብስቡ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፦ አንድ ስንኳ እንዳይጠፋ የተረፈውን ቍርስራሽ አከማቹ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 6:12
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም፥ “ሂዱ፤ የሰ​ባ​ው​ንም ብሉ፤ ጣፋ​ጩ​ንም ጠጡ፤ ለእ​ነ​ዚ​ያም ምንም ለሌ​ላ​ቸው እድል ፈን​ታ​ቸ​ውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌ​ታ​ችን የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ላ​ችን ነውና አት​ዘኑ” አላ​ቸው።


ምሽ​ጎ​ቹ​ንም ከተ​ሞች፥ መል​ካ​ምን ነገር የሞ​ሉ​ትን ቤቶች፥ የተ​ማ​ሱ​ት​ንም ጕድ​ጓ​ዶች፥ የወ​ይ​ኖ​ቹ​ንና የወ​ይ​ራ​ዎ​ቹን ቦታ​ዎች፥ ብዙ​ዎ​ቹ​ንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፤ በሉም፤ ጠገ​ቡም፤ ወፈ​ሩም፤ በታ​ላቅ በጎ​ነ​ት​ህም ደስ አላ​ቸው።


በሥራው ራሱን የማያድን፥ ራሱን ለሚያጠፋ ወንድም ነው።


የተ​ራ​ቡ​ትን ከበ​ረ​ከቱ አጠ​ገ​ባ​ቸው፤ ባለ​ጠ​ጎ​ች​ንም ባዶ እጃ​ቸ​ውን ሰደ​ዳ​ቸው።


ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ያ ትንሹ ልጁ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ በዚ​ያም በመ​ዳ​ራት እየ​ኖረ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ በተነ፤ አጠ​ፋም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “መጋቢ የነ​በ​ረው አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ እን​ደ​ሚ​በ​ትን አድ​ር​ገው በእ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ሱት።


ሁሉም በል​ተው ጠገቡ፤ ያነ​ሡ​ትም የተ​ረ​ፈው ቍር​ስ​ራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞላ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስና ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች