Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 5:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አብ ከቶ በማ​ንም አይ​ፈ​ር​ድም፤ ፍር​ዱን ሁሉ ለወ​ልድ ሰጠው እንጂ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ አሳልፎ ሰጥቶታል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 አብ ከቶ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ይልቁንም፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጥቶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22-23 ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 5:22
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ አለ፥ በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራራ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነውና።


አንተ ጐበዝ፥ በጕ​ብ​ዝ​ናህ ደስ ይበ​ልህ፥ በጕ​ብ​ዝ​ና​ህም ወራት ልብ​ህን ደስ ይበ​ለው፥ በል​ብ​ህም መን​ገድ፥ ዐይ​ኖ​ች​ህም በሚ​ያ​ዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለ​ዚህ ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ፍርድ እን​ዲ​ያ​መ​ጣህ ዕወቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራን ሁሉ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም ነገር ሁሉ፥ መል​ካ​ምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመ​ጣ​ዋ​ልና።


ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።


ሥጋ በለ​በ​ሰው ሁሉ ላይ ሥል​ጣ​ንን እንደ ሰጠ​ኸው መጠን ለሰ​ጠ​ኸው ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ።


አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና፥ ሁሉን በእጁ ሰጠው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ የሰው ልጅ ነውና ይፈ​ርድ ዘንድ ሥል​ጣ​ንን ሰጠው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የማ​ያ​ዩት እን​ዲ​ያዩ፥ የሚ​ያ​ዩ​ትም እን​ዲ​ታ​ወሩ ወደ​ዚህ ዓለም ለፍ​ርድ መጥ​ቻ​ለሁ” አለው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሕ​ያ​ዋ​ንና በሙ​ታን ላይ ፈራጅ ሆኖ የተ​ሾመ እርሱ እንደ ሆነ ለሕ​ዝብ እና​ስ​ተ​ምር ዘንድ አዘ​ዘን።


በመ​ረ​ጠው ሰው እጅ በዓ​ለም በእ​ው​ነት የሚ​ፈ​ር​ድ​ባ​ትን ቀን ወስ​ኖ​አ​ልና፤ እር​ሱን ከሙ​ታን ለይቶ በማ​ስ​ነ​ሣ​ቱም ብዙ​ዎ​ችን ወደ ሃይ​ማ​ኖት መል​ሶ​አ​ልና።”


ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እኔ በወ​ን​ጌል እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ርሁ ሰዎ​ችን በል​ቡ​ና​ቸው የሰ​ወ​ሩ​ት​ንና የሸ​ሸ​ጉ​ትን በሚ​መ​ረ​ም​ር​በት ጊዜ የሚ​ና​ገ​ሩ​ትና የሚ​መ​ል​ሱት እን​ደ​ሌለ ስለ​ሚ​ያ​ውቁ ነው።


መል​ካም ቢሆን፥ ክፉም ቢሆን በሥ​ጋ​ችን እንደ ሠራ​ነው ዋጋ​ች​ንን እን​ቀ​በል ዘንድ፥ ሁላ​ችን በክ​ር​ስ​ቶስ የፍ​ርድ ዙፋን ፊት እን​ቆ​ማ​ለ​ንና።


በእግዚአብሔር ፊት፥ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ፤


ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች